Get Mystery Box with random crypto!

ለእግዜር ' ' ደግ መሆንን ኑሬ ሰው መሆንን ልማር ቤትህ ጋር አኑረኝ በምህረትህ ልዳር ሰርጌን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ለእግዜር
'
'

ደግ መሆንን ኑሬ ሰው መሆንን ልማር
ቤትህ ጋር አኑረኝ በምህረትህ ልዳር

ሰርጌን ደግስልኝ የነፍሴን መካን
በራሴ ላይ ጭነህ
በቅዳሴ አንደበት በዜማ ቤት ልካን

ባሪያ ልሁን እና ፍቅርን ማተብ ላርገው
ለተጣላም ልኬው ወንጌል የማደርገው

መልሰኝ በዓለም ሰኮና ሳልጠፍ
ከበግ ልምድ ወጥቼ  ከተኩላ ሳልሰፍ

የጥምቀት ጨረቃን ድብዝዙን እኔን
ከፀሀይ አድርሰው ሳይጥል የራስ አይኔን

አሜን....!

ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19