Get Mystery Box with random crypto!

ወይ ጥጋብ! ተርባለች ብለው ሲያዝኑልሽ አይቼ በአገልግሌ ሙሉ አልጫና ቀዩን አንድ ላይ ፈትፍቼ በ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ወይ ጥጋብ!

ተርባለች ብለው ሲያዝኑልሽ አይቼ
በአገልግሌ ሙሉ
አልጫና ቀዩን አንድ ላይ ፈትፍቼ
በቅመም በእንቁላል በደንብ አጣፍጬ
በመልክተኛየ
ከፍቅር ፖስታ ጋር አብሬ ላኩልሽ
እህል እስክትቀምሽ
አፌን አልሽር ብየ እኔም ተራብኩልሽ!

ታርዛለች ብለው ሲከፉ አየሁና
በሻንጣየ ሙሉ
አልባሳት ሞላሁት ቢሸፍን ገመና
ይሄን ኮተት ሁሉ
በመልክተኛየ
ከፍቅር ፖስታ ጋር አብሬ ላኩልሽ
ልብስ እስክደርቢ
ብርድ አልፈራ ብየ እኔም ታረዝኩልሽ!

ተጠምታለች ብለው ሲያሙልኝ ሰምቼ
በዕቃየ በሙሉ
በባልዲ በሀይላንድ በስኒ ሞልቼ
በመልክተኛየ
ከፍቅር ፖስታ ጋር አብሬ ላኩልሽ
አንጀትሽ እስኪርስ
ውሀ አልቀምስም ብየ እኔም ጥም ሞትኩልሽ!

አሁን በተራየ
በአካላቴ ሁሉ
በአይን በጆሮየ በነፍሴ እንደያዝኩት
ልቤን ረጋ በል እስክንደርስ እያልኩት
መልክተኛ አስትተሽ ራሴን አስላክሽኝ
መልስሽ ግን ይገርማል
ፍቅር እንኪ ብልሽ 'ጠግቤአለሁ' አልሽኝ

ወይ ጥጋብ!

የተራበ እህል
የተጠማ ውሀ
የበረደው ልብሱን እየደራረበ
ማባበል ተስኖት
ማስታገሻ ላጣው ይብላኝ ለጠገበ!


             በአቤኒ የተጻፈ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19