Get Mystery Box with random crypto!

(አይዞን ጨረቃዬ,,,,,) ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠ ጥበብ ፈልቃ ፈልቃ  ፀሐይ ደምቃ ደምቃ ከጨረሰች | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

(አይዞን ጨረቃዬ,,,,,)
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ጥበብ ፈልቃ ፈልቃ 
ፀሐይ ደምቃ ደምቃ
ከጨረሰች ወዲህ ቦታዋንም ለቃ
ለ ...ጨ   ረ    ቃ

ምስኪኗ ጨረቃ በኮከቦች ደምቃ ጨለማን አብርታ
ትክ ብዬ ሳያት የኔን ይመስለኛል ህይወቴን ሕይወቷ

የኔ ምስኪን አንቺ
ያንቺ ምስኪን እኔ
ነይ እንተዛዘን ነዪ ጨረቃዬ
አልቃሽ አንፈልግም,,,, እኛው እንበቃለን
ሲመጡ አመስግነን ሲሔዱ እንሸኛለን

አይዞሽ ጨረቃዬ
እኔም ያንቺ አይነቷ አዛኟ ለራሴ
ሲመጡ መቀበል
ሲሔዱ መሸኘት
ለምጄ በነፍሴ
ያለቅጥ ምተክዝ ያለ አዛኝ ምባዝን
ያንቺ አይነቷ ምስኪን አለሁኝ በምድር

አይዞሽ ጨረቃዬ አይዞን,,,,

#Lidiya_y

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19