Get Mystery Box with random crypto!

እኩል ነው የሸጥነው ' ' በመምጫሽ ጊዜ ድግሱም አሰልች፣ አብሮ አደግ እንቦሳ ተሰረገ ለአንች ' | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እኩል ነው የሸጥነው
'
'
በመምጫሽ ጊዜ ድግሱም አሰልች፣
አብሮ አደግ እንቦሳ ተሰረገ ለአንች
'
'
ስሰክር በንዴት

አስቤማ ነበር፥ ጠላ በጆክ ይዘን ፣
አስቤማ ነበር ፥ ቋንጣ ስጋ ሰርቀን ፣
አስቤማ ነበር ፥ከሜዳው ጨለማ በጨዉ ለዋውሰን፣
አስቤማ ነበር ፥በሃሳብ ጎራርሰን ፣
ያራቀን ገደሉ ለሜዳ እንዲያደርሰን፣

'
'
አስታውሽ እቴዋ ልንበላው ያሰብኩት በሬ
እኩል አብሮ አድጓል ሳልከዳው ለዛሬ

ያኔ እምቦሳ ነበር ካንቺ ጋር ስተሻሽ
እኩል ቦርቀናል እረኛ ቤት ሲዋሽ
'
'
በገዛ ሰርግሽ ላይ ሰርግሽን ሳጠና ፣
የኔ ያልኩት በሬ፥ ለገንዘብ ሸጥኩት ባላባት ያዝሽና ፣

ይሁን አልኩ'

ባል'ሽ አንቺን ገዛሽ ፥እኔንም በሬዬን፣
እስከሸጡ ድረስ፥ ሁሉም ያስገምታል ብበላ ቋንጣዬን ፣
ለሰርግ አለመቅረት
ሁለት ብሰርግ ነው የሸጥኩት ዕንባየን፣

እያልኩ እያየውሽ፥ ደብቄ አልሰድር፣
ታዲያ እኔ አልወቅስሽ
እኩል ነው የሸጥነው በሬን እና ፍቅር፣
'
'

ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19