Get Mystery Box with random crypto!

Blaze Movement

Logo of telegram channel blazemovement — Blaze Movement B
Logo of telegram channel blazemovement — Blaze Movement
Channel address: @blazemovement
Categories: Telegram , Religion
Language: English
Subscribers: 1.62K
Description from channel

Blaze Movement is an annual international youth movement. It gathers the youth from around the world for a one month program which is concluded by huge musical concert at you go church. @ab_hailu

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages 2

2022-06-02 13:31:18 የመንፈሳዊ አገልግሎት መሠረታዊ መርሆዎች

(ከለፈው የቀጠለ)

1. መሥዋዕትነት - ምዕራፉ "ሰውነታችሁን... መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ" በማለት ይጀምራል። መሥዋዕትነት መሞትንና ሙሉ የሆነ መሰጠትን የሚያመለክት ቃል ነው። እዚህ ላይ የተጠቀሰው መሥዋዕትነት የመቀደስና ለአገልግሎት የሚሆን መሠጠት ነው።

መሥዋዕት ማቅረብ የካሕናት አገልግሎት ነው። የአዲስ ኪዳን ምዕመናን የንጉሥ ካሕናት ናቸው። የሚያቀርቡት መሥዋዕት ግን የእንስሳት አይደለም። የሚያገለግሉት ለእግዚአብሔር "መንፈሳዊ መሥዋዕትን"፣ በማቅረብ ነው። (1ጴጥ 2:5-9) ምዕመናኑ እንደ ካሕናት፣ በእግዚአብሔር ፊት፣ እንስሳትን ማቅረብ ባይጠበቅባቸውም የራሳቸውን "ሰውነት" ግን ያቀርባሉ።

የቀድሞው ሰውነት፣ ኃጢአትን የሚያገለግልና የአመጻ የጦር ዕቃ የነበረ ነው(ሮሜ 6:13፣19)። የአሁኑ ለጽድቅ አገልግሎት የተቀደሰ፣ ተለይቶ በመሥዋዕትነት የቀረበ፣ መሆን አለበት። መሥዋዕትነት ተመልሶ እንደቀድሞው ላለመሆን መሞትንም ያመለክታል። ታዲያ፣ ሞቱን በሚመስል ሞት ከክርስቶስ ጋር ያልተባበረ (ሮሜ 6:2-8)፣ ለኃጢአት ያልሞተ፣ ከኃጢአትም ባርነት ነጻ ያልወጣ፣ አያገለግልም ።

የሚያገለግል በአንድ በኩል ስናየው የታሠዋ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሕያው ሆኖ የሚኖር ነው(12:1)። ክርስቶስ ያገለገለን ቤዛችን በመሆን፣ በምትካችን ገብቶ በመሞት፣ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በመሠዋት ነው። ሞታችንንም በመሻር፣ ከሙታንም በመነሣት ግን በሕያውነት ለዘላለም ይኖራል። እኛ እንደ ምዕመናን ለኃጢአት ብንሞትም፣ በክርስቶስ በኩል ለጽድቅ ሕያዋን ሆነን፣ በመሰጠት ልናመልከውና ልናገለግለው፣ ሰውነታችንን ለእግዚአብሔር እናቀርባለን።

እውነተኛ አገልግሎት በአደባባይ ቆሞ ከመስበክም ከመዘመርም፣ ከመምራትም፣ ከሌላውም እንቅስቃሴ ያልፋል። በፍቅር ላይ የተመሠረተ መሥዋዕትነትን፣ መሰጠትን ይጠይቃል። ጌታ ኢየሱስ፣ "የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፣ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። " ብሏል። (ዮሐ 12:24) የሚሰበከውም ሆነ የሚዘመረው ወንጌል ውጤታማ የሚሆነው በመሥዋዕትነት ሕይወት፣ በሙሉ መሰጠት ሲቀርብ ነው።

በዘመናት ውስጥ ለወንጌል ጉዳይ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ የሰውነት ክብር፣ ጉልበትና ከዚያም ያለፈ፣ በፍቅር መሥዋዕትነት ቀርበዋል። ይህን በሐዋርያቱ አገልግሎት ውስጥም እንመለከታለን። የኖሩበትን ጽፈውታል። መርሁ ዛሬም አልተለወጠም። ያው ነው።

ማገልገል የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸምና እርሱን ደስ ማሰኘት ነው(ሮሜ 12:2)። አስቀድሞም ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ፣ እግዚአብሔር አብ;- "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ" የሚል ምስክርነት እንደሰጠው እናውቃለን። (ማቴ 3:17) ጌታ ኢየሱስም ዘወትር ደስ እንደሚያሰኘው በራሱ ቃል አረጋግጦታል። እንዲህ በማለት:-“... እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም... ።” ደስ ማሰኘቱ የቤዛነት ሞቱን፣ ራሱን "የመዓዛ ሽታ" አድርጎ ማቅረቡን ያጠቃለለ መሆኑም እሙን ነው ።( ዮሐንስ 8፥29። ኤፌ 5:2) ፈቃዳችንን በመተው፣ ፈቃዱን እየፈጸምን፣ ደስ ማሰኘት በአገልግሎታችን ልንከተለው የሚገባን የክርስቶስ ፈለግ ነው።

መልካሙ ምሳሌያችን ጌታ ኢየሱስ "የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ" ብሏል። (ዮሐ12:26) መከተል፣ መማርም ያስከተለውን መምሰልም ነው። ከሁሉም ይልቅ፣ ሕይወታችን ያስከተለንን ክርስቶስ በመምሰል፣ በሙሉ መሰጠት፣ እንደ ጸጋውም ብዛት፣ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበትን የጽድቅ አገልግሎት የምንሰጥበት ይሁንልን።

እውነተኛ የሆነው መንፈሳዊ አገልግሎት፣ በመሥዋዕትነት፣ ከመቀበልም ይልቅ በመስጠት ጌታን የምናከብርበት፣ እኛም የምንባረክበት ነውና (የሐዋ 20:35)።

(ይቀጥላል)
124 views10:31
Open / Comment
2022-05-31 13:07:50 የመንፈሳዊ አገልግሎት መሠረታዊ መርሆች

በሮሜ መዕራፍ 12 ላይ የተመሠረተ መጠነኛ ምልከታ

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ ውስጥ፣ አማኞች በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት፣ በክርስቶስ በኩል ስላገኙት ጽድቅና መዳን እያብራራ ቆይቶ፣ በዚህ ክፍል ውስጥ ስለ አገልግሎት ያወሳል። በተለወጠ ልብ (አስተሳሰብ)፣ በትሕትናና በፍቅር ዝንባሌ ማገልገል የዚህ ምዕራፍ ቀዳሚ ሐሳብ ነው ለማለት ይቻላል። ምዕራፉ በተለያየ መልክ ስለሚሰጥ አገልግሎት ይናገራል።

ማገልገል የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ነው። በመሆኑም፣ ፈቃዱን ማወቅ ይጠይቃል። ራስን በመሥዋዕትነት አቅርቦ በማምለክም ይጀመራል። (12:1-2) ማምለክና ማገልገል ተዛማጅነት ያላቸው አሳቦች ናቸው። ማምለክም ማገልገልም ዓላማው እግዚአብሔርን ማክበር ነው። ማምለክ/ማገልገል ለተቀበልነው ምሕረት የምንሰጠው ምላሽም ነው።

በሌላ ሥፍራ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ከተሰጠን ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ባለመታከት የምንሰጠው አገልግሎት እንዳለን ይገልጻል። (2ቆሮ 4:1) ከዚህ አገልግሎት ጋር ተያይዘው ሊታሰቡና እንደ ቀላል ነገር ሊታዩ የማይገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች (መርሆች) አሉ። በሮሜ ምዕራፍ 12 ላይ በመመሥረት የሚከተሉትን በጥሞና ብንመለከታቸው:-

1. መሥዕትነት- ሙሉ የሆነ መሰጠት(12:1) ፣
2. የታደሰ ልብ - ከዓለማዊነት የራቀና- የተለወጠ(12:2)
3. የትሕትና ዝንባሌ - ራስን ያለመካብ፣ በራስ አለመመካት(12:3)
4. የአካልነት ግንዛቤ - ከቤተ ክርስቲያን ጋር የተቆራኘ ማንነት(12:4-5)
5. የጸጋ ስጦታን መለየት - በተገቢው ቦታ ብቻ መሰለፍ(12:6-8)
5. በአገልግሎት መትጋት - አለመለገም፣ አለመስነፍ(12:7፣11፣13፣16)
7. ቃልና ተግባርን ማጣጣም - የተገለጠ ፍቅር (12:6-20)

(ይቀጥላል)
207 views10:07
Open / Comment
2022-05-14 15:00:10
“I surrendered unto Him all there was of me; everything! Then for the first time I realized what it meant to have real power.”

— Kathryn Kuhlman
220 views12:00
Open / Comment
2022-05-12 11:01:41 የመባረክ መንገድ
መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ
(ኤርምያስ 17:7)

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ሚያዝያ 30 /2014 ዓ.ም የተካሄደው የእሁድ የጉባኤ የዝማሬ፣ የፀሎት ፣ አምልኮ እና የቃል ጊዜ
በዕለቱ በነበረው የቃል አገልግሎት መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ ያገለገሉ ሲሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢተ ኤርምያስ ምእራፍ 17 ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መሰረት በማድረግ "የመባረክ መንገድ" በሚል ርዕስ ቀጥለው በቀረቡት ነጥቦች ላይ አስተምረዋል።

መባረክ በእግዚአብሔር ፊት የስኬት ይሁንታ ማግኘት (ይሁንልህ መባል) ነው። በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ ስኬቱ የሚገለጠው በዋናነት በቁሳዊ መልክ ነበር። በማሕጸን ፍሬ፣ በጤንነትና፣ በብልጥግና መልክ ማለት ነው። ሰላምን (ደኀንነትንም) ይጨምራል (ዘዳ 7:15፣ 28:1-14)። ይህም እግዚአብሔርን በታማኝነት ከማምለክና ለእርሱ ከመታዘዝ ጋር በጥብቅ የተያያዘ ጉዳይ ነው። የመግቢያው የንባብ ክፍላችን እንደዚህ ዓይነት በረከት የሚገኝበትን መንገድ ያሳያል።

ምዕራፉ የይሁዳ ሕዝብ የነበረበትን መንፈሳዊ ውድቀት በማውሳት ይጀምራል። ውድቀታቸው ጠለቅ ያለ ነበር። የእግዚአብሔር ሕግ ሊቀመጥበት በሚገባው የልባቸው ጽላት ኃጢአታቸው ተጽፎ ነበር። ኃጢአታቸው ለሕያው እግዚአብሔር የሚደረገውን ብቸኛና እውነተኛ አምልኮ በጣዖት አምልኮ የተካ ነበረ። ይህ ኃጢአት ወደ ቀጣዩም ትውልድ ዘልቆ ሊታሰብ የሚችል (አእምሯቸውን የሚይዝ) ሆኗል። የዚህ ኃጢአት ውጤት በእጃቸውና በደጃቸው የተቀመጠውን እግዚአብሔርን በረከት ሊያጡ የሚችሉበት ነበር።

"ባለጠግነትህንና መዝገብህን ሁሉ... ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለመ'በዝበዝ እሰጣለሁ" ይላል(17:3)። በዚህ ሃሳብ መነሻነት ቃሉ ስለ መባረክ መንገድ ሁለት ዓይነት ሰዎችን በማነጻጸር ያስተምረናል።
አንደኛው በሰው የሚታመን፣ ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ፣ ልቡ ከእግዚአብሔር የሚመለስና "ርጉም" የተባለው ነው። ይህ ሰው፣ በምድረ በዳ እንዳለ ቁጥቋጦ፣ መልካምም በመጣ ጊዜ እንደማያይ፣ ሰው በሌለበት፣ ጨውም ባለበት፣ በምድረ በዳ፣ በደረቅ ሥፍራ እንደተቀመጠ ሰው ሆኖ ይታያል(17:5-6)።

ሁለተኛው ሰው፣ በእግዚአብሔር የታመነ፣ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነና "ቡሩክ" የተባለ ነው። ይህ ሰው፣ በውኃ አጠገብ በተተከለ፣ በወንዝም ዳር ሥሩን በሚዘረጋ፣ ሙቀትም ሲመጣ በማይፈራ፣ ቅጠሉም በሚለመልም፣ በድርቅ ዓመትም በማይሰጋ፣ ፍሬውም በማይቀቋረጥ ዛፍ ተመስሏል (17:7-8)። ንጽጽሩ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንድን ያስታውሰናል።

በዚህ የንባብ ክፍል ውሰጥ፣ የመባረክም ሆነ የመረገም(ያለመባረክ) መንገዱ በእግዚአብሔር ከመታመን ወይም ካለመታመን ጋር እንዴት እንደተያያዘ በግልጽ እንመለከታለን። በእግዚአብሔር መታመን፣ እርሱን ብቻ በታማኝነት በማምለክና ለእርሱ በመገዛት የሚገለጽ የጠራ አቋም ነው።

በአዲስ ኪዳን፣ መባረክ በክርስቶስ በኩል የሚገኝና በዓይነቱ ሰማያዊነትና መንፈሳዊነት ያለው ነው። ይኼኛው በረከት፣ ከዚያኛው የሚበልጥ ስለሆነ፣ ዋጋው እጅግ የላቀ ነው። "... በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም"(ሮሜ 8:1)። ይልቁንም፣ "በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በሰማያዊ ሥፍራ፣ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ" የተባረኩ ናቸው (ኤፌ1:3)።

እንግዲያውስ፣ ሰማያዊውን በረከት ከምድራዊው፣ መንፈሳዊውን በረከት ከቁሳዊውና ከአላፊው፣ መለየት ያስፈልገናል። ለመንፈሳዊውና ለዘላለማዊው በረከትም ዋጋ ልንሰጥ የገባናል። ለጊዜውም ቢሆን፣ ቁሳዊው ነገር ለምድራዊው ኑሯችን ሊያገለግለን እንደሚችል አይካድም። ይሁን እንጂ፣ ይህ ነገር፣ ተጨማሪ እንጂ ዋና እንዲሆን፣ ቁሳዊውም ሀብት ቀልባችንን እንዲቆጣጠረው፣ በፍጹም መፍቀድ የለብንም። የእግዚአብሔር ቃል፣ "ይህን ሲመኙ፣ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ስቃይ ራሳቸውን ወጉ" እንደሚላቸው እንደ "አንዳንዶች" እንዳንሆን ልንጠነቀቅ ይገባናል(1 ጢሞ 6:10)።

የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን ቁሳዊ ብልጥግናዋን የምታውጅ፣ ክርስቶስን ግን ገፍታ ወደ ደጅ ያወጣች፣ በክርስቶስም ዓይን ምስኪንና ጎስቋላ ሆና የምትታይ ደሀና ዕውር ነበረች። ከእንደዚህ ዓይነት መንፈሳዊ ጉስቁልና ሊያወጣንና እይታችንን ለመፈወስ ዛሬም ጌታ ጥሪውን ያቀርብልናል (ራዕ 3፣17-18)።
በሥጋ ለባሽም ሆነ በቁሳዊ ድጋፍ፣ ወይም በሌላ ነገር ተመክተን፣ በነፍሳችን ጠውላጋ ከመሆን፣ ሕይወት የለሽም ሆኖ ከመቅረት እንጠበቅ። ልባችን የሕይወት ምንጭ ከሆነው ከሕያው አምላክ፣ ከእግዚአብሔር ወደ ኋላ አይመለስ። ከዳተኞች አንሁን። የእውነተኛና የዘላቂ በረከት መንገዱ፣ የዓለም መድኃኒት የሆነው፣ እኛንም ለማዳን በምትካችን ገብቶ የሞተው፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ይህን በውል እንገንዘብ። ዘላለማዊውን በረከት ለመውረስ በክርስቶስ ላይ እንደገፍ። የሚስፈልገንን ሁሉ ራሱ ይሞላብናል። አኛ ግን ዋናውን ዋና እናድርግ። የመባረክም ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው።

ከላይ የቀረቡትን ነጥቦች ትኩረት በመስጠትና በማብራራት በስብከታቸው መጨረሻ ለጉባኤው ፀሎት ተደርጎ የፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆኗል፡፡

Follow Us
YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
Telegram
https://t.me/hawassafullgospelch
Facebook
https://facebook.com/FGBCHawassa

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ስነፅሁፍና ስነዳ አገልግሎት
ሚያዝያ 30 /2014 ዓ.ም
149 views08:01
Open / Comment
2022-04-22 10:47:58
344 views07:47
Open / Comment
2022-04-18 09:45:44
#Good_Friday

ዓርብ ሚያዝያ 14
11:30 (Local time)
ዩጎ ቸርች
𝕁𝕖𝕤𝕦𝕤 𝕀𝕤 𝕄𝕠𝕣𝕖 𝕋𝕙𝕒𝕟 𝔼𝕟𝕠𝕦𝕘𝕙!
507 viewsedited  06:45
Open / Comment
2022-04-13 15:17:30

494 views12:17
Open / Comment
2022-03-20 15:54:44
You can follow this bot to buy the album

@SelamLemdrachenAlbumBot
764 views12:54
Open / Comment
2022-03-18 11:00:50

669 views08:00
Open / Comment