Get Mystery Box with random crypto!

*በምያንማር የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ እና የፕላስቲክ ጥይቶችን በመተኮስ ጉዳት | DW Amharic

*በምያንማር የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ እና የፕላስቲክ ጥይቶችን በመተኮስ ጉዳት ማድረሱ ተገለጠ። የምያንማር መንግሥት ቴሌቪዥን ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን በተንቀሳቀሰበት ወቅት ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰልፈኞች ዛሬ ዘግቧል። የምያንማርን ሲቢላዊ መንግስት አስወግዶ ሥልጣን የያዘዉን ወታደራዊ ኹንታ የሰጠዉን ማስጠንቀቂያ በመጣስ ተቃዋሚዎች የጀመሩት ሰልፍ አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። ዛሬ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፈኞች አደባባይ መውጣታቸው ተዘግቧል። ሰልፈኞች በወታደራዊ ኹንታው ከሥልጣናቸው የተወገደዉ የሐገሪቱ መንግሥት ወደ ሥልጣን እንዲመለስ እየጠየቊ ነው።

የዓለም ዜናውን ሙሉ ዘገባ በድምጽ እዚህ https://p.dw.com/p/3p8F6?maca=amh-RED-Telegram-dwcom ማድመጥ ይቻላል።
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ደግሞ ይኽን ይጠቀሙ @dwamharicbot