Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንግስት የአውሮጳ ሕብረት «በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ነው» በማለት ያወጣ | DW Amharic

የኢትዮጵያ መንግስት የአውሮጳ ሕብረት «በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ነው» በማለት ያወጣውን መግለጫ ነቀፈዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር እንደሚለዉ የሕብረቱ መግለጫ መንግሥት በክልሉ እያቀረበ ያለውን የሰብዓዊ ርዳታ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው።የአውሮጳ ሕብረት ትናንት ባወጣው መግለጫ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ዉስጥ መግባት እና በክልሉ እየተፈጠረ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ አሳስቦኛል ብሎ ነበር።የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ለሕብረቱ መግለጫ በሰጠዉ መልስ "መንግሥት በአካባቢው የሕግ ማስከበር ስራን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሕብረቱ የሚያወጣው መግለጫ ሚዛናዊነቱን ያልጠበቀ እና ተገቢነት የሌለው ነው" ሲል ወቅሷል። የአውሮጳ ሕብረት ትናንት እውጥቶ በነበረው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢያዎች ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ እና ለስደተኞችና ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቋል።የመንግስታቱ ድርጅት 25 የዕርዳታ አቅራቢ ሰራተኞች ወደ ትግራይ ክልል እንዲገቡ ከኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ ማግኘቱን አስታዉቋል።የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር <<የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በበርካታ የትግራይ ክልል ተደራሽ እንዲሆን መንግሥት እየሰራ ነው>> ብሏል::
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በትግራይ ክልል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ 4.5 ሚሊየን ሕዝብ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልገዋል :: ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት በክልሉ የተረጂዎችን ቁጥር ከ2.5 ሚልዮን እንደማያልፍ ሲገልፅ ቆይቷል::