Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ1,500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመ | DW Amharic

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ1,500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዘገበች:: እትሌቷ በሀገሯ ልጅ ገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንዶች በማሻሻል 3:53:09 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው አሸናፊ የሆነችው:: በፈረንሳይዋ የሌቪን ከተማ ትናንት ማምሻውን በተደረገው የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ሌሎች ኢትዮጵያውያንም አሸናፊዎች ሆነዋል:: አትሌት ለምለም ሀይሉ በ3,000 ሜትር ርቀት አሸናፊ ስትሆን በወንዶች ተመሳሳይ ርቀት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው በመግባት እሸናፊዎች ሆነዋል:: ውድድሩን ጌትነት ዋለ 1ኛ በመውጣት አሸንፏል::