Get Mystery Box with random crypto!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ መተከል ዞን ለተፈጠረው ሰብአዊ ቀውስ በይፋ ይቅር | DW Amharic

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ መተከል ዞን ለተፈጠረው ሰብአዊ ቀውስ በይፋ ይቅርታ ጠየቀ:: ፓርቲው ካለፈው እሁድ ጀምሮ ሲያካሂድ የነበረውን ኮንፈረስ ዛሬ ካጠናቀቀ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫው "በሠላምና መረጋጋት ዕጦት ስትጠቀስ ማስተዋል በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የደረሰው ሞትና መፈናቀል ልብ ሰባሪ መቼም እና የትም መደገም የሌለበት አሳዛኝ ድርጊት በመሆኑ መላ የክልላችንን ኗሪዎች ይቅርታ እየጠየቅን በተግባር ለመካስ መዘጋጀታችንን እናረጋግጣለን" ብሏል፡: ነገር ግን በክልሉ የደረሰው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጥፋት ዝርዝርን በተመለከተ እንዲሁም ለተጎጂዎች ሊደረግ ስለሚገባ ዝርዝር የካሳ ሁኔታ ፓርቲው ያለው ነገር የለም:: ከዚህ ቀደም በዞኑ ለሚፈጠሩ ችግሮ የተለያዩ ምክንያቶች ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን የክልሉ መንግስት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቋዋሚ ፓርቲዎችን እና ግብጽን ተጠያቂ ሲያደረጉ ነበር፡፡