Get Mystery Box with random crypto!

ኬንያ ከሶማልያ በምትዋሰንበት ሰሜናዊ ክፍል የአሸባብ ታጣቂዎች እያደረሱ ነው የተባለውን ጥቃት ተ | DW Amharic

ኬንያ ከሶማልያ በምትዋሰንበት ሰሜናዊ ክፍል የአሸባብ ታጣቂዎች እያደረሱ ነው የተባለውን ጥቃት ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ነው:: በእካባቢው ማንዴራ የተባለች ግዛት እስተዳዳሪዎች እንዳስታውቁት የታጣቂዎቹን ጥቃት በመስጋት 126 ት/ቤቶች አሁንም ድረስ አልተከፈቱም:: በአካባቢው ታጣቂዎች በመንገድ ዳር እያደረሱ ያለውን የቦምብ ጥቃትን በመስጋት መምህራን እና ተማሪዎች ወደ ት/ቤት መሄድ አለመቻላቸው ተገልጿል:: በግዛቲቱ የሚገኙ ጎዳናዎች በታጣቂዎቹ እጅ መውደቃቸው ለጥቃቱ መባባስ አስተዋጽዖ ማበርከቱም ተነግሯል:: ታጣቂዎቹ መንገደኞችን ያስጨንቃሉ :: የመንግስት ሰራተኞች ደግሞ ዋነኛ ትኩረታቸው መሆኑ ተገልጿል:: በተጨማሪም ታጣቂዎቹ ለእጅ ስልኮች ኔትወርክ የሚያቀርቡ ማማዎችን ማውደማቸው ችግሩን እንዳባባሰው የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል:: ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት አሸባብ ኬንያ ኢትዮጵያ እና ሶማልያ በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ሀይሉን እያጠናከረ መምጣቱ ተዝግቧል::