Get Mystery Box with random crypto!

*በሚያንማር ወታደራዊ የመንግሥት ግልበጣው ዐሥረኛ ቀኑን ካስቆጠረ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ብርቱ ር | DW Amharic

*በሚያንማር ወታደራዊ የመንግሥት ግልበጣው ዐሥረኛ ቀኑን ካስቆጠረ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ብርቱ ርምጃ እንደምትወስድ ገለጠች። በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱ የተሳተፉ ጄኔራሎች እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው የሆኑ ድርጅቶች ላይ አሜሪካ የማዕቀብ ቅጣት እንደምትፈጽም ዝታለች። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን፦ በእስር ላይ የሚገኙት የኖቤል ተሸላማሚዋ አውንግ ሳን ሱ ኪ እንዲፈቱ፤ ሀገሪቱም ወደ ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንድትመለስ አሳስበዋል። በመላ ሀገሪቱ ወታደራዊ አመራሩን በመቃወም ዛሬም በዐሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች አደባባይ ወጥተዋል። ከሚናምማር ውጪም የተቃውሞ ሰልፎች ተከናውነዋል። ጃፓን ውስጥ በተደረገ ሰልፍ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰብ ለሳን ሱኪ እና ደጋፊዎቻቸው አለኝታነታቸውን ዐሳይተዋል። «የሚያንማር ጦር ሠራዊ አመራር ምን ያህል መጥፎ እንደሆነ ለዓለም እንነግራለን። ለሳስን ሱ ኪ መልእክቴ፦ በአንድነት ለመተባበር ተግተን እየሠራን ነው፤ ተስፋ እንዳይቆርጡ የሚል ነው። እሳቸውም ወታደራዊ አገዛዙን እስኪያሸንፉ በርቱ ተስፋ አትቊረጡ።» በሚያንማር መዲና ናይፒይዳው የጦር ሠራዊቱ ላይ ጫና ለማሳደር በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ መሐንዲሶችም ዛሬ የተቃውሞ ሰልፉን መቀላቀላቸው ተዘግቧል። በመላ ሀገሪቱ የተቃውሞ ሰልፉ ዛሬ ስድስተና ቀኑን አስቆጥሯል።

*የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የመከሰስ መብትን ለማንሳት ለሁለተኛ ጊዜ የተጀመረው ሒደት ሦስተኛ ቀኑን ዛሬ አስቆጥሯል። ዶናልድ ትራምፕ በመዲናዪቱ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ፓርላማ ሕንፃ ላይ ለደረሰው ኹከት ተጠያቂ ናቸው ለማለት ዴሞክራቶች ጫፍ መድረሳቸውም ተዘግቧል። ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ለኹከት እንዲነሳሱ ያደረጉበት የተባለ የቪዲዮ ምስል ትናንት በማስረጃነት ቀርቧል። የዶናልድ ትራምፕ ጠበቆች የቀድሞው ፕሬዚደንት ምርጫው ተጭበርብሯል ብለው ለማወጅ የመናገር ነጻነት አላቸው ሲሉ ተከራክረዋል። ዴሞክራቶቹ ዶናልድ ትራምፕን ለመክሰስ አጠቃላይ 50 ዴሞክራት ሴናተሮች እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፓርቲ የሪፐብሊካን አባላት ከሆኑት 50 ሴናተሮች የ17ቱ ድምፅ ያስፈልጋቸዋል።

*ቲክቶክ የተሰኘው የቪዲዮ ምስሎች ማጋሪያ የማኅበራዊ መገናኛ ዘርፍ የቀጣዩ የአውሮጳ ዋንጫ ስፖንሰር እንደሆነ የአውሮጳ እግር ኳስ ማኅበራት ኅብረት (UEFA) ይፋ አደረገ። ውድድሩን በገንዘብ በመደገፍ ቲክቶክ አራተኛው የቻይና ድርጅት ኾኗል። ቲክ ቶክ የአውሮጳ የእግር ኳስ ዋንጫን ለመደገፍ ምን ያህል ገንዘብ እንደበጀተ ግን አልተገለጠም። የ2020 አውሮጳ እግር ኳስ ዋንጫ በኮሮና ተሐዋሲ ስርጭት ለአንድ ዓመት መራዘሙ ይታወቃል።

የዓለም ዜናውን ሙሉ ዘገባ ማድመጥ እዚህ https://p.dw.com/p/3pEjw?maca=amh-RED-Telegram-dwcom ይቻላል። አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot