Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ውጥረት በውይይት መፍታት እንደሚገባ የሁለቱ አገሮች ምሁራን | DW Amharic

በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ውጥረት በውይይት መፍታት እንደሚገባ የሁለቱ አገሮች ምሁራን ገለጡ፡፡ ከሱዳን የመጡና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በባሕር ዳር ባደረጉት ውይይት የተፈጠረውን የድንበር ጉዳይ በጦርነት መፍታት ዘላቂ መፍትሔ የለውም ብለዋል። ለመፍትሄው ውይይት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ታሪክ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አይቸግረው አደራ እንዳሉት የድንበር ጉዳይ የሁለቱ አገሮች ችግር ብቻ እንዳልሆነ አስታውሰዋል ። ቅኝ ገዥዎች የፈጠሩት ችግር የብዙ አፍሪካ አገሮች ተግዳሮትና የግጭት ምንጭ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ የሰሩት በወሎ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር መምህር ዶ/ር ዓለማየሁ እርቅይሁን በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ችግር በውይይት መፈታት አለበት፣ ያ የሚሆነው ግን ሱዳን ወደነበረችበት ስትመለስ ብቻ ነው ብለዋል፡፡ በሱዳን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የስነጥበብ ፕሮፌሰር ዶ/ር ኡመር አላሚን በበኩላቸው ሁለቱም አገሮች ህዝቦቻቸውን ወዳልተገባ ሁኔታ የሚወስዱ ሽፍቶችን ማስወገድ አለባቸው ሲሉ ለዶይቼ ቬከ ገልፀዋል፡፡