Get Mystery Box with random crypto!

የሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ ርዕሶቹ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል «በሰላም የ | DW Amharic

የሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል «በሰላም የተመለሱ » ከ100 በላይ ታጣቂዎች አፈንግጠው ጫካ መግባታቸው ተገለጸ። ላለፉት ሁለት ወራት ያህል ከነትጥቃቸው በግልገል በሰለስ ከተማ አቅራቢያ የሰፈሩት ታጣቂዎቹ ተመልሰው ዱር መግባታቸውን የከተማዋ ከንቲባ አረጋግጠዋል።
• የግሪክ ድንበር ጠባቂዎች 100 ፍልሰተኞችን ከባሕር መስጠም መታደጋቸውን ዐስታወቁ። ፍልሰተኞቹን በማጓጓዝ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳትፎ ነበራቸው የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
• በአንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም ባለስልጣን ላይ ግድያ የፈጸመ ግለሰብ መለየታቸውን የየመን የጸጥታ ባላስልጣናት ዐስታወቁ ። ባለስልጣናቱ ገዳዩን ደረስንበት ይበሉ እንጂ ግለሰቡ ከጂሃዲስቶች ወገን ይሁን አይሁን በግልጽ ያሉት ነገር የለም።
• ሩስያ በጥቁር ባህር ከተደረሰው የእህል ዝውውር ስምምነት መውጣት «ሚሊዮኖችን ለረሃብ እና ለከፋ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል» የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኃላፊ አሳሰቡ።
• ዩክሬን ፤ ሩስያ በኃይል በያዘቻት የክሬሚያ ግዛት በአንድ የጥይት ማከማቻ መጋዘን ላይ ባደረሰችው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ በባለስልጣናት ታዘዙ ።
• ትናንት ዓርብ ሞናኮ ፈረንሳይ ውስጥ በተከናወነ የዳይመንድ ሊግ የሩጫ ውድድር በ5000 ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን ወንዶች ተከታታለው በመግባት ከ1ኛ እስከ3ኛ ያለውን ደረጃ ሲቆጣጠሩ ፤ በሴቶች አንድ ማይል ርቀት ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፒገን አዲስ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ ችምር አሸናፊ ሆናለች። https://p.dw.com/p/4UGm4?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot