Get Mystery Box with random crypto!

​‍ የጠፋው ሬሳ ምዕራፍ ሁለት ክፍል ደራሲ፡-የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ...... | Emoji feelings🦋

​‍ የጠፋው ሬሳ
ምዕራፍ ሁለት
ክፍል

ደራሲ፡-የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር)


.........ራሴን እንዴት እንዳሰብኩት ለኔም ግራ ነው፡፡ ነፍሴን ለማትረፍ ለኔው ብቁ ያልሆንኩ ሰው እሷን ለማዳን እታትራለሁ፡፡ "ሰው መሆን እንዲ ነው" ይለኛል ውስጤ ሊያጀግን እንዳሰበ ሁሉ፡፡ "አዎ ሰው ማለት ከራስ አልፎ ሌላ ሲኖር ነው የተከበሩ የዓለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ "አንተ ራስህን ሲያምህ ከተሰማህ በህይወት አለህ ማለት ነው፡፡ሌሎች ሲታመሙ አንተ ከተሰማህ አንተ በትክክል ሰው ነህ ማለት ነው" ይላል እናም ልክ ነው በጣም ልክ፡፡

እናም ካለኝ አቅም ይልቅ ሰውነቴ አሸንፎኛል፡፡ ባላድናትም ላድናት ማስናለሁ አልተዋትም፡፡ ስቃዯ ውስጤ ዘልቆ ሲሰማኝ ይታወቃኛል፡፡ የቤቱ ቁር ለጉድ ነው፡፡ ወደ መውጫው ተጠጋሁና ኮሪደሩን አንገቴን አስግጌ ቃኛሁ በማን አለብኝበት ፀጥታ ፍፁም ነግሶበታል፡፡ ግድግዳውን እየታከኩኝ እንደ ድጋፍ ተመርኩዤ አዘግም ጀመር፡፡ የምሄድበትን አውቀዋለሁ ወይ እዛው ቀራለሁ ወይ እመለሳለሁ፡፡ ከዚ ሌላ ምንም ሊፈጠር አይችልም፡፡ ይሄንን አበክሬ አስቤዋለሁ፡፡ በየ አስር እርምጃዎቹ የተለያዩ ክፍሎች ይገኛሉ ክርፋታቸው የከረመ ሬሳ ብስባሽ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

የመጀመሪያውን ክፍል አልፌ ሁለተኛውጋ ስደርስ ከአንድ ጠረጴዛ ላይ ከሰውነት ላይ የተለያዩ የሰው አካል ክፍሎች ተሰድረዋል፡፡ በፍጥነት ተራምጄ አለፍኩት አሁን የማያቸውን አረመኔያዊ የሰው ልጅ ስቃዬን ሳይ ለመድኩት መሰል ወይ ደግሞ ያንን ክፉ ለመግደል ስላላመነታሁ አሰጨከነኝ እንደሁ እንጃ እንደበፊቱ አያሸብረኝም፡፡

ጥቂት ክፍሎችን እየቃኘሁ ከተጓዝኩ በሗላ የሴትየዋንና የሴቲቱን ክፍል ከሩቅ ቃኘሁት፡፡ ትኩር ብዬ ተመልክቼ አንዳች እቅስቃሴ በውስጡ አለመኖሩን ተረዳሁ፡፡ ግን ወደክፍሉ ከማምራቴ በፊት የሰዎቹን ሁናቴ ማጤን እንዳለብኝ ተረድቻለሁ፡፡ እነሱ ያሉበት ስፍራ እኔ ካለሁበት በስተጀርባ ካሉት ክፍሎች አንዱ ውስጥ ናቸው፡፡ የትኛው ክፍል እንደሆነ ግን በውል አለየውም፡፡ ሆስፒታሉ ሰፊና ትንሽ ፅልመት የወረሰው በመሆኑ ያደናግረኝ ይዟል፡፡

"እስካሁን እኔን ፍለጋ ስለምን አልመጡም?"ወይንስ እያዘናጉኝ ይሆን?"
አላውቅም ይሄ ለኔ ግድ አይሰጠኝም ከባርሳ ነፍስ ይልቅ፡፡ እኔ የነበርኩበትን ኮሪደር አልፌ በጀርባ ወዳሉት ክፍሎች የሚወስደውን መተላለፊያ ይዤ በዝጋታ እና በንቃት ሁናቴያቸውን ለማጤን ሞከርኩ፡፡ ግን ዘለግ ላለ ግዜ ለራሴ እስኪጨንቀኝ ፀጥ ብለዋል፡፡

ከደቂቃዎች በሗላ ንግግር አይሉት መልጎምጎም የሆነ የጎረምሳ ድምፅ ይሰማል፡፡ የዛኔ አረመኔ ድምፅ ነው ስቃይ ምን ማለት እንደሆነ በትንሹ ቢሆን እየተጎነጨው ነው፡፡ ጊዜ ሳላጠፋ በቀጥታ ወደ ክፍሉ አመራሁ፡፡ እግሬ ፈፅሞ ሰላም እየነሳኝ ነው፡፡ ቢሆንም ባልችም እችላለሁ፡፡ እልህ እያንጨረጨረኝ በቀል ውስጤን እያነደደ ነው፡፡

በሩን በርግጄ ገባሁ በቀጥታም መቁረጫውን አገኝ ዘንድ ከወዲያ ወዲህ ባተትኩ ግን አልነበረም፡፡ እቃዎቹን አተረማመስኳቸው የትም አልነበረም፡፡ በጣም ተበሳጨው፡፡ ወደ ሌላኛው ክፍል ገባሁ ሁለት አልጋ የያዘ ነበር፡፡ይመስለኛል የሴቶቹ ነው፡፡ በአንዱ አልጋ ትራስጌ በኩል ሁለት መንታ የሚመስሉ ህፃናት ፎቶ አለ ከጎናቸው ደግሞ መልከ መልካም ወጣት የተመረቀበት ምስል ይታያል፡፡ "እዚህ ስፍራ ላይ ይህ ፎቶ የማን አምሳያ ይሆን? የሁለቱ ጨቅላ ፎቶስ ምንድነው ትርጉሙ?" እያልኩ ራሴን ጠይቃለሁ መልስ እንደማገኝ ሁሉ፡፡

ግድግዳው ላይ ደግሞ በጥሩ ሀኔታ የተያዘ ሙሉ ሱፍ ተሰቅሏል፡፡ነገሮች የባሰ እየማረቱ ሄዱ፡፡ የማየው ሁሉ ጥያቄ እንጂ መልስ አልነበረውም፡፡ ፎቶዎቹ ወደተቀመጡበት ስፍራ ተጠጋሁ፡፡ አጠገባቸው ሌላ አልበም ተቀምጧል፡፡

ያለማንታት ብድግ አድርጌ አነሳሁት፡፡ የመጀመሪያው ገፅ ላይ አንድ ትንሽ ህፃን መለመሉን ተንጋሎ ሲስቅ ያሳያል፡፡ ትንሽ ፈገግ አስባለኝ፡፡ ቀጣዩን ገለጥኩት፡፡ አሁንም እርቃኑን በደረቱ ተኝቷል አስቀድሜ ያየሁት ድንቡሽቡሽ ቆንጅዬ ብላቴና፡፡ ግን ያየሁት ነገር አስደነገጠኝ፡፡
"ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?" ብዬ ራሴን ጠየኩ፡፡

ያየሁት ነገር ይበልጥ ግራ አጋባኝ፡፡ መቼም ገጠመኝም አጋጣሚም ሊሆን እንደማይችል እርግጥ ነው፡፡ ይሄን ጥያቄ ማን ሊመልስልኝ ይችላል ማንስ ያብራራልኛል?፡፡ የመጣሁበት ዓላማ እስክዘነጋ ድረስ ፈፅሞ ተቆጣጥሮኛል፡፡ የሰማሁት የቁራ ድምፅ ባያነቃኝ ኖሮ፡፡

ለዛ አረመኔ እንደ አደጋ ጥሪ መሆኑ ገብቶኛል የቁራው ጩኸት ከዚህ በሗላ ያለኝ ደቂቃ ትንሽ ነውና ተፋጥኜ መውጣት አለብኝ፡፡ አልበሙን ከነበረበት መልሼ የመኝታ ክፍሉን ለቅቄ ልወጣ ስል ጉጠት መሳዩ መቁረጫ ወለሉ ላይ ተቀምጦ አገኘሁት፡፡ "መርፌ ሚፈልግን ሞፈር ቢያነድለው...ይላል ተረቱ ልክ ነውም፡፡ እንደዛ አተራምሼ ያሰስኩትን ስተወዉ አገኘሁት፡፡

አነሳሁትና እያነከስኩኝ ክፍሉን ለቅቄ ልወጣ ስል...ይቀጥላል

እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን እንደ ላይክ ብዛት እንፈጥናለን