🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቨርቹዋል ሪያሊቲ -1 - Part One ምናባዊ ምስለ-እውነታ - ቨርቹዋል ሪያሊቲ (Virtua | Ethio biruks app @ ኢትዮ ብሩክስ አፕ

ቨርቹዋል ሪያሊቲ -1 - Part One

ምናባዊ ምስለ-እውነታ - ቨርቹዋል ሪያሊቲ (Virtual Reality)(VR)

ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ማለት አሁን ካለንበት የገሀዱ ዓለም አውጥቶ ወደ ሌላ የዲጅታል ዓለም የሚዘፍቅ (Immerse) አስደናቂ ቴክኖሎጂ ነው።

ለምሳሌ እናንተ ቤታችሁ ውስጥ ናችሁ እንበል ወይም ቢሮ ውስጥ ወይም ታክሲ ውስጥ ናችሁ...ወዘተ....ባጭሩ አሁን ካላችሁበት ቦታ ሳትንቀሳቀሱ በህይወታችሁ "ባየሁት!" ወይም "ባደረኩት!" ብላችሁ ወደ ምትመኙት ዓለም መጓዝ ብትመኙስ? ወይም

አሁን ካላችሁበት ቦታ ሳትንቀሳቀሱ በአራዊቶች የተሞላ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ውስጥ መሆን ብትፈልጉስ? ሜድትራኒያን ባህር ውስጥ ከሻርኮች ጋር መዋኘት ብትመኙስ?....ወይም ደግሞ አውሮፕላን ማብረር ብትፈልጉ...

ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ካላችሁበት ዓለም ሳትንቀሳቀሱ ወደ ተመኛችሁት ዓለም የሚወስድ እጅግ አስደናቂ ቴክኖሎጂ ነው። ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ከላይ በምስሉ እንደምትመለከቱት እንደ መነፅር ዓይናችን ላይ የምናጠልቀው መሳሪያ (Head-mounted Device) ያስፈልገናል።