2022-06-12 18:33:51
Programming language
Programming language ማለት ከ ኮምፒዉተር ጋር ሊያግባባን የሚችል program ለመፃፍ የሚጠቅም ቋንቋ ማለት ነው: :
Computer ላይ የምንጭናቸው ማንኛውም አይነት የ ዳታ አይነቶች ለምሳሌ: photo, video , software....ሌሎችም የሚቀመጡት Mechine language በሚባል 0 እና 1 ቁጥሮች በያዘ የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : ለምሳሌ 10 ቁጥርን ከ keyboard ብናስገባ ኮምፒዉተራችን የሚረዳውና የሚያስቀምጠው ወደ እንደዚህ አይነት ቁጥሮች ቀይሮ ነው 010001010...እነዚህ አይነት ቁጥሮች Machine language በመባል ይጠራሉ: :
Machine Language
━━━━━━━━━━━━━
Machine language ማለት computer ሊረዳው የሚችል የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : የሚጠቀመውም 0 እና 1'ን ብቻ ነው: : ለምሳሌ 33 በ Machine language 00100001 ነው: :
➠ ነገር ግን ለኛ ለሰዎች Machine language'ን ለማንበብና ለመረዳት ከባድም አሰልቺም በመሆኑ ምክንያት በ Machine language program መፃፍ የማይታሰብ ነው: :
➠ በዚም ምክንያት ሰዎች አንብበው ሊረዱት የሚችል program መፃፊያ ቋንቋ(programming language) ለመፍጠር ጥረት መደረግ ተጀመረ: :
ይህ ጥረትም ለ Assembly language መፈጠር ምክንያት ሆነ: :
Assembly Language
━━━━━━━━━━━━━━
Assembly language ሰዎችንና computer'ን በመጠኑም ቢሆን ያቀራረበ ቋንቋ ነው: :
Assembly language ከ Machine language አንፃር ለማነበብና ለመረዳት በመጠኑም ቢሆን ቀለል ያለ programming language ነው: :
Assembly language የእንግሊዝኛ ፊደላትን የያዙ አጫጭር ቃላቶችን ይጠቀማል። ለምሳሌ: ADD, MUL, MOV, INC, POP, PUSH, SUB, DEC,....,e.t.c
እነዚህ Assembly language ላይ ያሉ አጫጭር ቃላት(instructions) mnemonic( ሜሞኒክ) ተብለው ይጠራሉ።
Assembly language እና Machine language ባንድ ላይ low-level programming language በመባል ይጠራሉ: :
Assembly language ከ Machine language አንፃር ለ ሰው ልጅ ቋንቋ ቀረብ ያለ ነው አልን እንጂ እሱም ቢሆን ለ መማንበብ እና ለመረዳት ያን ያህል የቀለለ አልነበረም: :
በዚህም ምክንያት እስካሁን ካየናቸው የተሻለና ለማንበብ ለመፃፍ የበለጠ የቀለለ አዲስ programming language አስፈለገ: :
High-level Programming language
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
➻ በፈረንጆቹ ወደ 1950ዓ.ም ላይ ለ ሰውልጅ ቋንቋ እጅግ የቀረበ, እንግሊዘኛ ቋንቋ መሳይ ለማንበብ , ለመረዳት እና ለመፃፍ ቀላል የሆኑ programming language'ኦች መሰራትና ወደ ገበያ መውጣት ጀመሩ: : እነዚህ programming language'ኦች high-level programming language በመባል ይታወቃሉ: :
➻ አሁን ባለንበት ዘመን ከ 100 በላይ High-level programming language'ኦች ይገኛሉ: : ከነዚህ ውስጥ ታዋቂዎቹ:
C, C++, C#, Java, COBOL, FORTRAN, Python, PHP …ይገኙበታል: :
━━━━━━━━━━━━━━━
26 views15:33