🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#ኢትዮጵ #በናይል_ላይ_የተፈፀሙ_ስምምነቶች በናይል ዙርያ ላይ የተከናወኑ ውሎችና ስምምነቶች በ | ኢትዮጵ

#ኢትዮጵ


#በናይል_ላይ_የተፈፀሙ_ስምምነቶች
በናይል ዙርያ ላይ የተከናወኑ ውሎችና ስምምነቶች በዋነኛነት በቅኝ ገዢዎች የተከናወኑ ሲሆን ግብጽን ማእከል ያደረጉና ሌሎች ተፋሰስ ሀገራትን የሚያገሉ ብሎም ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ የናይል ወንዝ የቅኝ ገዢዎች ቀልብና ፍላጎት መሳብ የጀመረው ከ19ኛ መክዘ ጀምሮ ነው፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ እንግሊዝ የናይል ወንዝን አጠቃቀምና አጠባበቅን በማስመልከት ስምንት ስምምነቶችን ተፈራርማለች፡፡ እንግሊዝ ለምን ይህን ያህል ስምምነት በናይል ወንዝ ላይ መዋዋል አስፈለጋት የሚለውን ጥያቄ ስናይ እንግሊዝ የግብፅ ቅኝ ገዥ ስለነበረች በአንድም በሌላ መንገድም የራሷን ጥቅም እያሰከበረች ነበር፡፡ ሌሎች የቅኝ ገዥ ሀገራትም በናይል ወንዝ ዙርያ ሲያከናውኑዋቸው የነበሩት ስምምነቶች የራሳቸውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማጎልበት እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ ይሁንና የእነዚህ ስምምነቶች ትሩፋቶች የግብፅ ብሄራዊ ጥቅም ብቻ የሚያስከብሩና የሌሎች ተፋሰስ ሀገራት ጥቅም ታሳቢ ያላደረጉ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ከ1891 እስከ 1959 ድረስ በናይል ወንዝና ገባሪዎቹ ላይ የተከናወኑ ስምምነቶች እንደሚከተለው እንያቸው፡፡

#የ1891_የጣልያንና_የእንግሊዝ_ስምምነት

ይህ ስምምነት የግብፅን ጥቅም ላለመንካት ሲባል ጣልያን በአትባራ ወይም ተከዜ ወንዝ ላይ ግድብ እንደማትሰራ ከእንግሊዝ ጋር የተዋዋለችበት ነው፡፡ በውሉ አንቀፅ 3 ላይ እንደሰፈረው ጣልያን የናይል ገባር ወንዝ የሆነውና ከአዲስቷ የቅኝ ተገዥ ኤርትራ ግዛት ላይ የሚነሳውን አትባራ ወንዝ ላይ የመስኖ ወይም የውኃውን ፍሰት የሚቀንስ ማንኛውም አይነት ስራ እንደማትሰራ ከእንግሊዝ ጋር ውል ማድረጓን ያሳያል፡፡ ጣልያን ከሃፀይ ዮውሀንስ መስዋእትነት በኃላ እ.ኤ.አ. ከ1890-1941 የኤርትራ ቅኝ ገዥ እንደነበረች የሚታወስ ሲሆን ይህ ውል ፍፁም ኢ-ፍትሀዊና በምን አገባኝ ስሜት የተፈፀመ መሆኑን መገመት የሚከብድ አይደለም፡፡

#የ1901_የእንግሊዝና_የጣልያን_ስምምነት

ይህ ስምምነት ከደቡባዊ አስመራ ተነስቶ አትባራ ወንዝን የሚገብርና በመጨረሻም ወደ ናይል የሚቀላቀል ጋሽ/መረብ ወንዝን በማስመልከት በእንግሊዝና በጣልያን መካከል የተከናወነ ሲሆን ይዘቱም ኤርትራ በመልካም የጉርብትና መርህ ላይ ተመስርታ በወንዙ ላይ የመጠቀም መብት እንዳላት እውቅና የሚሰጥ በመሆኑ ከሌሎች የቅኝ ገዢዎች ስምምነቶች በተሻለ ሁኔታ ፍትሀዊና የአሁኗ ኤርትራን መብት የማይጎዳ ነው ይባላል፡፡

#የ1902_የእንግሊዝና_የኢትዮጵያ_ስምምነት

ይህ ስምምነት ግንቦት 15 ቀን 1902 እ.ኤ.አ የሱዳን ቅኝ ገዥ በነበረችው በእንግሊዝ እና በኢትዮጵያ መካከል የተከናወነ የአዲስ አበባ የድንበር ስምምነት ነበር፡፡ ይሁንና በዚሁ ስምምነት አንቀጽ 3 ላይ መነሻቸው ከኢትዮጵያ ያደረጉ የናይል ገባሪ ወንዞችን የሚመለከት የውኃ ስምምነት ይዘትም ተካትቶበታል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ንጉስ ሚኒሊክ በግዛቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የእንግሊዝና የሱዳን መንግስታት ፈቃድ ሳያገኝ የአባይን ወንዝ ፍሰትን ማስቆም የሚችል ማንኛውም አይነት ስራ እንዲሰራ የማይፈቅድ መሆኑን የተስማማበት ውል ነበር፡፡ ይህ ውል የኢትዮጵያ መንግስት ሳይገደድና በራሱ ፍላጎት ስምምነቱን የፈረመበት በመሆኑ ኢትዮጵያ የምትገደድበት ውል ነው የሚል በግብፅ በኩል ክርክር ይነሳል፡፡
የስምምነቱ አንቀፅ 3 የእንግሊዝኛና የአማርኛ ቅጂዎች በተከታታይ እንደሚከተለው እንያቸው፡፡

“His Majesty the Emperor Menelik II, King of kings of Ethiopia, engages himself towards the Government of His Britannic Majesty not to construct or allow to be constructed, any works across the Blue Nile, Lake Tana or the Sobat, which would arrest the flow of their waters into the Nile except in agreement with his Britannic Majesty�s Government and the Government of the Sudan�.
ጃንሆይ ዳግማዊ ምንይልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ከጥቁር አባይና ከባህረ ፃና ከሰባት ወንዝ ወደ ነጭ ዐባይ የሚወርደውን ውሀ ከእንግሊዝ ጋር አስቀድመው ሳያስማሙ ወንዝ ተዳር እዳር የሚደፍን ስራ እንዳይሰሩ ወይም ወንዝ የሚደፍን ስራ ለመስራት ለማንም ፈቃድ እንዳይሰጡ በዚህ ውል አድርገዋል፡፡"

ይህ ውል የኢትዮጵያ ሉአላዊነትን የሚነካ አወዛጋቢ ይዘት ያለው ቢመስልም አሁንም ግን ህጋዊነቱን ውድቅ ለማድረግ የሚጠቅሙ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑንም በብዙ የውሀ ሕግ ልሂቃኖች የሚታመንበት ነው፡፡ ለምሳሌ አንደኛ ውሉ በእንግሊዝም ሆነ በኢትዮጵያ አልፀደቀም ወይም Ratify አልተደረገም፡፡ ይሁንና ከዚህ ጋር ተያይዞ በወቅቱ የሁለትዮሽ ሆነ የባለብዙ ወገን ስምምነቶችን ማጽደቅ የሚችል የተለየ ተቋም ባልነበረበት ሁኔታ ስለ ውሎችን መፈረም እንጂ ስለማፅደቅ የሕግ ክርክር ሆኖ መነሳት የለበትም የሚል የመልሶ ማጥቃት ክርክርም ይነሳል፤ምክንያቱም እንደአሁኑ ዘመን የስልጣን ክፍፍል የሚደግፍ ህጋዊ መርህ ባልነበረበት በተለይም ደግሞ ሕግ አውጪ፣ ሕግ አጽዳቂና ሕግ ትርጓሚ ራሱ ንጉሱ በሆነበት ሁኔታ የሁለትዮሽ ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልፀደቀ ተቀባይነት የለውም የሚለውን ክርክር ውሀ የሚያነሳ አይደለም በማለት ይከራከራሉ፡፡

ሁለተኛ በእንግሊዘኛውና በአማርኛው መካከል የቃላት አለመጣጣምና የትርጉም መጣረስ አለበት፤በአማርኛው ቅጂ የኢትዮጵያ መንግስት የማሳወቅ ግዴታ የገባው እንግሊዝን ብቻ ሲሆን በእንግሊዘኛው ቅጂ ላይ ግን ሱዳንም ተጨምራለች፡፡ ይህ የአማርኛ ቅጂ የኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት መገለጫ ነው ተብሎ የሚታሰበው እንግሊዝ ሱዳንን ትታ እስክትሄድ ድረስ የሚቆይ ጊዚያዊ ግዴታ መግባቱን ነው፤ለዚሁ ማሳያም በውሉ አንቀፅ 4 ላይ “ለቅቆ እስኪሄዱ” የሚል የአማርኛ ቃልና “Removed” የሚል የእንግሊዘኛ ቃል እናገኛለን፡፡ በሌላ በኩል ውኃውን Arrest ወይም Block ማድረግን ወይም ሙሉ በሙሉ ማስቆምን እንጂ ማንኛውም አይነት ተጠቃሚነትን የሚከለክል ውል አይደለም፡፡ ዞሮ ዞሮ የውሉ የአማርኛ ቅጂ ከእንግሊዘኛው በተሻለ ሁኔታ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር ቢሆንም የውሉ የእንግሊዘኛው ቅጂም ኢትዮጵያ ወንዟን ከመጠቀም የማይከለክላትና እንግሊዝ ሱዳንን ለቃ ከሄደች በኃላም የውሉ ተፈፃሚነትን የሚያበቃ በመሆኑ ኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ ይህን ውል የምትቀበልበት የሕግ ምክንያት የለም፡፡ ግብፅም የውሉ 3ኛ ወገን እንጂ ፈራሚ ባለመሆኗ ይህን ውል በማንሳት መከራከር አትችልም፡፡

ጽንሰ ኢትዮጵያ ሐዳስ


#ለማንኛውም ሐሳብ እና አስተያየት
@Yottor_bot
ላይ ያድርሱን።