Get Mystery Box with random crypto!

.................... ፩ ...................... .... ' ተመልሳ | ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ

.................... ፩ ......................
.... " ተመልሳ ስትሄድ ከጀርባዋ አይዋት። እንደሀረግ እጥፍጥፍ የሚል ወገብና ዛላ። ከሽከሽ ቀሚሷ ስር ባቶቿን ተመለከቱ።
እንደብዙዎቹ በአንቀልባ ታዝለው የሚያድጉ ሰሜነኛ ልጆች ባት አልቆጠረችም።
ይህቺ ብቻ ነበረች ቅሬታቸው። የደነገጠች ልባቸው ወደ ቦታዋ ለመመለስ ጊዜ ወሰደባት።
ጠጁን ደጋግመው ተጎንጭተው መመገብ ጀመሩ። አይኖቻቸው ግን ወደ ጀርባው በር እንደተተከሉ ቀሩ። ትንሽ ቆይተው ሴትየዋ ወደ ጀርባ ተጣሩ።
" ውባ.....ንች!..... ውባ...ንች!" አቤት ስትላቸው "ቡናውን አምጭ!"አሏት።
ሻንበል መንግስቱ ይሄኔ ደስ ብሏቸው ቁንጥንጥ አሉ።
........... የቄሳር እምባ ገፅ 37 ..........
#የቄሳር_እምባ
ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው
በ2007 ዓ.ም በ408 ገፆች ተሰንዶ ለሁለት እውቅ ኢትዮጵያዊ ደራሲያን ማለትም ለአቤ ጉበኛና በ ግርማ በማስታወሻነት ተበርክቶ ለአንባቢያን የቀረበው የደራሲ ሀብታሙ አለባቸው አብዮት ተኮር ታሪካዊ ረጅም ልቦለድን ተተርሰን በጥቂቱ ልንቃኝ ወደድን እነሆ ፦
እንደመንደርደሪያ በሰማያዊው የደርግ ካኪ ስለተቀለዱ ቀልዶች ከመፅሀፉ ላይ ከየገፁ አይተን ፈገግ ብለን እንሻገር እነሆ አንድ :-
........ "በዓሉ እንደምታውቀው ነው። የኢንግሊዝ ሱፍ የጣሊያን ሸማዝና የቱርክ ከረባት ይለብሳል።
የሚረጨውን ሽቶም ታስታውሳለህ።በብዙ ነገሩ ምዕራባዊ ነው።
ሱፍ መልበስን ለእሱ ብቻ የተፈቀደ አድርጎታል። እኛ ሱፍ ስንለብስ ግን ተሳለቀብን።
" አብዮቱ ተቀለበሰ እንዴ ? " ብሎ አላገጠ።
ዳዊት ካኪ እንልበስ የተባባልን ጊዜ ምን እንዳለ ታውቃለህ ? " ጉዳዩ ከልብሱ አይደለም! "ብሎ አሾፈብን።....
............... ገፅ 8 - 9 ...........
ይላል አንድ ያጣላል እንድገም እስኪ :-
....... " ጨፌ በቃ ይሄን የደንብ ልብስ አልሞክረውም ብለህ ቀረህ አይደል? "አሉ ሻለቃ ደመቀን ሽቅብ አንጋጠው እየተመለከቱ። ከተዋወቁ ጊዜ ጀምሮ በሚጠሩበት ቅፅል ስም ጠርተዋቸው ፈገግታ አሳይተዋቸው።
" ጓድ መንግስቱ ምን ላድርግ ብለህ ነው? ሞክሬው ነበር።
ግን እሱን ስለብስ ራቁቴን የምሄድ ነው የሚመስለኝ።
ሙታንታ ብቻ እንደለበስኩ ነገር....."
አነጋገራቸው ኮሎኔሉን ፈገግ አሰኛቸው።......

የቄሳር እምባ
ከአጀማመሩ ጀምሮ የአንባቢን ልብ ሰቅዞ በማይንገጫገጭ ውብ ትውፊታዊ ፖለቲካ ቀመስ ታሪኮችን ሲያስዳስሰን እንመለከታለን ከደርግ ሊቀመንበር ጓድ መንግስቱ ሀይለማርያም የቤተመንግስት እንቅስቃሴ ባለቤታቸውን ወይዘሮ ውባንቺን እስካገኙበት ተራ የወታደርነት ሙያ ድረስ ወርዶ በማሰስ የመንግሰቱ ሀይለማሪያምን የግል ባህሪ ፣ የፖለቲካ አረዳድና ከባልደረቦቹ ጋር የሚግባባበትን ቋንቋ ታኮ በዚህ የልብ ወለድ ታሪክ ውስጥ እንደቅመም ከተጠቀመው ገፀባህርይ የመቶ አለቃ በላይነህ ጋር ያለውን የሞት ጥላ ያንጃበበበት ስውር የግንኙነት መስመርና ህዝብ ስለላን ጨምሮ በርካታ ነጥቦችን ልብ እንደሰቀለ እንደወራጅ ውሃ ሲወርድ በሌላ በኩልና የፈላጭ ቆራጩ የጅማው የደርግ ሹሙ ሚስት የአሰንዳቦው ቡና ነጋዴው ልጅ የሳቅ ንግስቷ የፈገግታ አድባሯ '
ሀምራዊትና የመንግስቱ ሀይለማርያም ስውር ሰላይና ባለ ብሩህ አእምሮው የፖለቲካ ተንታኝ የመቶ አለቃ በላይነህ ስውር ውሽምነት ድረስ ጠልቆ ሲመረምር መንግስቱ በአመራሩ ሰበብ በቤተሰቡ ላይ ምን አይነት ቀውስ እንዳስከተለ ለማሳየት የመንግስቱ የመጀመሪያ ልጅ ትምህርት መንግስቱ በገፅ _ ላይ እንዲህ ስትሆን እንመለከታለን:-_
..
.......ምን ሰምታ እንደተቆጧት ሲጠይቋት ነው ኮሎኔል ደመቀ ጋር ደጅ ቆመው የሰሟቸው።
"ይሄ የአሜሪካ ሬድዮ እያለ ምን ጤና አለ ብለህ ነው? ዳዊት ነው ማነው የሚባል ሰው አባቴን ሰደበው ብላ ስትቃጠል ነው አንተ የደረስከው።" ብለው ወይዘሮ ውባንቺ አገጫቸውን በእጃቸው ያዙ።
................... ገፅ 17.............
ሌላም አለፍ ብለን አንድ እንጨምርና ከዚህ ጉዳይ ወጣ እንበል
....." ትምህርት የወንድ ጓደኛ ይዛለች።ፈረንጅ ነው።ዜግነቱ ኖርዌይ ይሁን ኔዘርላንድ ትበለኝ አላውቅም ረስቼዋለሁ።
ለምን ፈረንጅ እንደመረጠች ጠየቅኳት። 'ታዲያ ሀበሻ አግብቼ አባቴን ሳሰድበው ልኑር?' ኢትዮጵያዊ አግብቼ ባኮረፈ ቁጥር አንች የነብሰ ገዳይ ልጅ ከሚለኝ ቆሜ ብቀር ይሻለኛል ' አለችኝ።
ትምህርት እንዲህ ስትለኝ እንባዬ መጣ ....በሷ ቦታ ሆነህ አስበው እስኪ..."
" ምን ታደርጊዋለሽ ፣ ሐምሪዬ... ውርስ እዳ ነው!!" ቅሬታዋ ወደ እሱም ተጋባበት።
................ ገፅ 250 - 251 .........
.....
ኮሎኔል መንግስቱ አይደለም ደፍሮ የተናገራቸውን ቀርቶ ሳት ብሎት ሀይለ ቃል ያመለጠውን ባለስልጣን በምን መንገድ እንደሚያስገድሉ የተኬደበትን መራር ግፍ ለማሳየት የእውቁ ደራሲ በዓሉ ግርማ እና የሌሎችንም ጀነራል ህይወት በከንቱ መንጥፋቱን ሲተርክልን መቶ አለቃ በላይነህ በገፅ 104 - 105 ከመቶ አለቃ ምስጋናው ጋር የሚያደርጉትን ትንፋሽ ቀጥ የሚያደርግ የሚስጥር ውይይት የመንግስቱ ሁለተኛዋ ሴት ልጅ ትዕግሥት መንግስቱ መጥታ እስካቋረጠችበት ድረስ እንዲህ......
...
...... " አዎ አንተ ከመጀመሪያው ድረስ አብረካቸው ነበርክ። ስንቱን መከራ አልፈሃል። ማዕረጉ ይገባሃል።
እነሱ በተጋጩ ቁጥር እርምጃ ወሳጅ መሆኑ በራሱ ከባድ ስራ ነው " ብሎ ወደ ትዕግሥት ገልመጥ አቀርቅራ እየሰራች አያት። በቀጥታ ወደ ነጥቡ ገባ " አንተ ሰባቱ ደርጎች ሲረሸኑ ጀምሮ ነበርክ አይደል? "
" ታዲያ! ጀነራል ተፈሪን ፣ ሻምበል አለማየሁ ና ሻምበል ሞገስን እኔ ነኝ የመታኃቸው።
ምን የመሰለ ድምፅ የሌለው ቶምሶን የሚባል የእስራኤል ጠበንጃ ነበረኝ መሰለህ። በእሱ ነው የመታኃቸው።
ኮሎኔል ኅሩይን ፣ ኮሎኔል አስራትን ፣ ሻምበል ተፈራንና አስር አለቃ ኃይሌን ደግሞ መቶ አለቃ ገብሩ ራሱ ነው የመታቸው።
እንዲያውም አስር አለቃ ሀይሌ በጀርባ ተገልብጠው በጫማ ጥፊ ሊመታቸው ሲታገሉ አየሁት።
እኔ የተመደቡልኝን ገድዬ ጨርሼ ነበር። ሄጄ ያዝኩለት። ማጅራቱ ላይ መታው። ሻለቃ አጥናፉንም እዛው ጋራዥ ውስጥ ምድር ቤት ነው የመታኃቸው።......
..
በሚል ተርኮ ሲያበቃ። ልክ በገፅ 138 ላይ ደሞ በሀምራዊት አንደበት ልብ የሚሰነጥቅ ጆሮን አቁሞ እንደሎጥ ሚስት የጨው አምድ ቀጥ የሚያደርግ ሽብርን ይነዛብናል እነሆ ከገፅ_ 138 ......
....... "በቀደም ለት አስመራ በሄድክ በሁለተኛው ቀን ሌሊት ..... ከቤቴ ጀርባ ድምፅ ሰማሁ። አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ይሆናል።
የሆነ ሰው ይጮሃል። 'በእግዜር ይዣችኃለሁ ተዉኝ ' እያለ ይለምናቸዋል። 'ምን ተፈጠረ ብዬ ደነገጥኩ።' ድምፁ እየራቀ እየራቀ ሄደ።
ትቼው ተመልሼ ጋደም አልኩ። ትንሽ ቆይቶ ሁለት ጥይት ተተኮሰ። ከርቀት በደንብ አይሰማም።
ከዚያ ሁሉም ነገር ፀጥ አለ።
ጧት ስራ ገብቼ አንድ በመኪና አደጋ የቆሰለ ወታደር መጣ።
ሳየው እንደገና ትዝ አለኝ። ' ገና በሌሊት ሶስተኛ ግቢ የምን ተኩስ ነው የሰማሁት? ' ብዬ ሲያቀብጠኝ ጠየቅኩት።
ለማንም እንዳትናገሪ ብሎ ' የጓድ መንግስቱ አጃቢ መቶ አለቃ ምስጋናው ተረሸነ' አለኝ።
" ተረ.........ሸ........ነ?" በላይነህ ጭንቅላቱን ይዞ ጉንዳን እንደነደፈው አይነት ተስፈንጥሮ ተነሳ።.....
....