Get Mystery Box with random crypto!

#በዋሽንግቶን_ዲሲ_የተካሄደው_ሰልፍ ከሰሞኑ በሺዎች የመቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ | ገራዶ ሚዲያ

#በዋሽንግቶን_ዲሲ_የተካሄደው_ሰልፍ

ከሰሞኑ በሺዎች የመቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በትግራይ ክልል እየደረሰ ነው ያሉትን ሰብዓዊ መብት ጥፋት፣ እና የመብት ረገጣ በመቃወም በዋሽንግቶን ዲሲ ሰልፍ አድርገው ነበር።

ሰልፈኞቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ዘር የማጥፋት ጦርነት ታውጇል ይህንን ነው የምንቃወመው ብለዋል፤ "ይህንን የምንለው እየተገደለ ያለው የፖለቲካ መሪ ብቻ ስላልሆነ፤ የሚገደሉት ንፁሃን ዜጎች ጭምር ስለሆኑ ነው" ሲሉ ይገልፃሉ።
አክለውም እየተሰደዱ እየተገደሉ፣ ንብረታቸው እየተቃጠለ እና እየተዘረፉ ያሉት ንፁሃን ናቸው ብለዋል።

በትግራይ ክልል ሴቶች እየተደፈሩ፣ እየተገደሉ ነው እነዚህ ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው ያሉት ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች እንጂ የTPLF አመራሮች አይደሉም ሲሉ ተናግረዋል፥ በዚህ ምክንያት ነው ዘር የማጥፋት ተግባር ነው የምንለው ብለዋል። እነዚህ ሰልፈኞች በትግራይ ክልል እየደረሰ ያለው በደል እንዲቆም የአሜሪካ መንግሥት ጣልቃገብነት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

የአሜሪካ መንግስት (የትራምፕ አስተዳደር) ጦርነቱን በይፋ ወጥቶ አልተቃወመም፤ የባይደን አስተዳደር ላይ ያሉ ሰዎች ግን ጉዳዩ እንደሚሳስባቸው እየገለፁ ነው ነገር ግን ይህ በቂ አይደለም ብለዋል።

የአሜሪካ መንግስት የውጭ ኃሎች ከትግራይ በአስቸኳይ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ እንዲያደርግ፣ ለሰብዓዊ ድጋፍ መንገድ ክፍት እንዲደረግ ጫና እንዲያሳድር እንጠይቀለን ብለዋል።

ከሰልፍ አስተባባሪዎች መካከል መኣዛ ግደይ፥ "በትግራይ ክልል ሰዎች እየተራቡ ያሉት ምግብ ስለታጣ አይደለም፤ መንገድ ነው የጠፋው፣ የትግራይ ተወላጆች ብር አዋጥተናል እጃችን ላይ ይገኛል፥ አለም አቀፍ NGO እርዳታ ይዘው እየተጠባበቁ ነው፤ አብይ አህመድ እና ደጋፊዎቹ መንገዱን አንከፍትም ስላሉ ህዝቡ ረሃብ አጋጥሞታል" ብላለች።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ሰልፉ በህግ ማስከበር ዘመቻችን ድል የተደረጉ አካላት ደጋፊዎች እና ተባባሪዎች የጠሩት፤ ብዙዎችን አሳስተው የመሩት ነው" ሲሉ ድርጊቱን አውግዘዋል።

ኣምባሰደር ፍፁም፤ በመንግስት ላይ እየቀረበ ያለውን የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ አድርገዋል። መንግስት ክልሉን ለማረጋጋት "ፅንፈኛው የህወሓት ኃይል" ያፈራረሳቸውን መሰረተ ልማቶች የመጠገን እና የነፍስ አድን ቁሳቁሶች የማድረስ ተግባር የኢትዮጵያ መንግስት እየሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

አክለውም መንግድት አሁን ላይ 92 ምግብና መድሃኒት ማሰራጫ ጣቢያዎች ወደነበሩበት መልሷል፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በየአካባቢው አስተዳዳሪዎችን እያስመረጠ እሰራ ነው ያለው፤ ለክልሉ ተገቢው ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።

አምባደር ፍፁም አረጋ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር በክልሉ ነዋሪዎች ላይ የመብት ረገጣ እየፈፀመ ነው ለሚለውም ክስ እንደማይቀበሉት ገልፀው የቀድሞ የህወሓት አስተዳደት ፈቶ በለቀቃቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የቀድሞ እስረኞሽ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር መንግስት እየሰራ ነው ብለዋል።

አምባሳደር ፍፁም፥ "...የኤርትራ መንግስት (በትግራይ ክልል ጉዳይ) ተሳትፎ እንዳልነበረው እራሳቸው መግለጫ ሰጥተዋል፤ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ለኤርትራ መንግስት የተደረገ ግብዣ እንደሌለ ከነሱ ጋር በመተባበር የተሰራ ስራ እንደሌለ በተደጋጋሚ ገልጿል። ሌላው የሚሰማው በርካታ ወንጀለኞችን ፈተው በመሄዳቸው ወደ 13 ሺህ የሚጠጉ እስረኞች ተፈተዋል ተብላል ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ወንጀሎችን ለመከላከል መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን ከፍተኛ ስራ እየሰራ ነው" ብለዋል።

"ከአሁን በፊት ከፍተኛ የሆነ ጭፍጨፋ በማይካድራ ተፈፅሟል፤ በማይካድራ የተካሄደው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትም ትልቅ አፅንኦት ሰጥተው ቀጣይ ምርመራ እየተደረገበት ነው ያለው። ሌላ ከዛ የተለየ ነገር በሌሎች አካባቢዎች በግጭቱ ያጋጠሙ ጉዳቶች ካልሆነ በስተቀር የሰማነው የለም። ነገር ግን መንግስት ለማጣራት ክፍት ነው። በመንግስት በኩል ይሄን ሆን ብሎ የሚያደርግበት ምንም ምክንያት የለውም፤ ዜጎችን ለማዳን እየሰራ ነው። ሁሉም ወገኖቻችን ናቸው። ግን እኛ ባልነው መንገድ ካልሆነ በስተቀር ሀገሪቱ ትፍረስ የሚል አቋም የያዙ ኃይሎች በሚዲያው በሶሻል፣ በመደበኛ ሚዲያው፣ ከፍተኛ የሀሰት ፕሮፖጋንድ በስፋት እየረጩ ነው ያሉት፤ እውነት እንደሆነ ይዘገያል እንጂ እያደር መጥራቱ አይቀርም" ብለዋል አቶ ፍፁም።

Via VOA, Compiled by #Tikvah

t.me/geradomedia