Get Mystery Box with random crypto!

የካይሮ ደላሎች ያሰናዱት አቤቱታ ለባይደን መንግስት (በእስሌማን አባይ - የዓባይ ልጅ) ግብፅ | ገራዶ ሚዲያ

የካይሮ ደላሎች ያሰናዱት አቤቱታ ለባይደን መንግስት

(በእስሌማን አባይ - የዓባይ ልጅ)

ግብፅ የቀጠረችው የጉዳይ እንደራሴ ተቋም ፀረ-ህዳሴ ግድብ አቤቱታ አደራጅቶ ለባይደን መንግስት ለማቅረብ ቀጠሮ ይዟል። የግብፅን ጉዳይ በእንደራሴነት የያዘው የሎቢ ኩባንያ ነው አዲሱን የአሜሪካ መንግስት ለማግባባት መርሃግብር ቀርፆ መድረክ ያዘጋጀው።

የህዳሴ ግድቡ አካባቢያዊ ተፅዕኖው እጅግ ከፍተኛ ነውና የባይደን መንግስት ይህን እንዲገነዘብ እንሰራለን እያለም ይገኛል፤ ኩባንያው። ለዚህም በዋሽንግተን የሚገኘው የግብፅ ኢምባሲ ነገ feb, 1 ባዘጋጀው የዙም ኮንፈረንስ ላይ ለማግባባት ተግባራቸው ይጠቅሙኛል ያላቸውን አካላት ተሳታፊ እንዲሆኑ የሎቢ ድርጅቱ ጥሪ አድርጓል። በኮንፈረንሱ የተሳታፊዎች መጥረያ ደብዳቤ ላይም የሎቢ ኩባንያው በነጩ ቤተ መንግስት አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚያተኩረው "International Conservation Caucus" ይቋቋም ዘንድ ከዋነኛ መስራቾች ውስጥ እንደነበረ አስታውሷል።

ነገ ሊካሄድ ባቀዱት ኮንፈረንስ ላይ የግብፅ መስኖ ሃይድሮሊክ ፕሮፌሰር ሒሻም በኪህ፣ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህግ አማካሪ ሙሐመድ ሂላል ተሳታፊ ይሆናሉ። ትራምፕ ተሸንፈው ጅጆ ባይደን ወደ ዋይት ሐውስ መምጣታቸውን ተከትሎ በየወሩ 65 ሺ ዶላር እየተከፈለው ለማግባባት ተግባር የተፈራረመውን Brownstein Hyatt Farber Schreck በፖሊሲ ዳይሬክተርነት የሚመራው Royce እንዲሁ የኮንፈረንሱ ተሳታፊ ናቸው።

t.me/geradomedia