🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#በማይናማር_የወታደሩ_ስልጣን_መያዝ በቀድሞ በርማ በአሁኗ ማያንማር ወታደሩ ሥልጣን መቆጣጠሩ ተሰ | ገራዶ ሚዲያ

#በማይናማር_የወታደሩ_ስልጣን_መያዝ

በቀድሞ በርማ በአሁኗ ማያንማር ወታደሩ ሥልጣን መቆጣጠሩ ተሰምቷል። ወታደሮች ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት የሲቪል መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

የኖቤል ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ተለቅመው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል። በማይናማር በወታደሩ እና በሲቪሊያን አስተዳደሩ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት ተከስቶ ነበር።

እነ ሳን ሱ ቺ ከመታሰራቸው ቀደም ብሎ የመንግሥት ቴሌቪዥን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ ነበር። ሚየንማር የዲሞክራሲያዊ ማሻሻያዎችን ማድረግ እስከጀመረችበት 2011 ድረስ በጥብቅ ወታደራዊ መንግሥት ነበር ስትመራ የቆየችው።

ባለፈው ሕዳር ወር በተደረገ ምርጫ የሳን ሱ ቺ ፓርቲ 'ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ' መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችለውን የመቀመጫ ቁጥር ማግኘት ችሎ ነበር። ሆኖም ወታደሮቹ ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ቆይተዋል።

በዛሬው ዕለት የሀገሪቱ ወታደሮች የአገሪቱን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውና መሪያቸውም ኮማንደር ሚነ ኦንግ ሌይንግ መሆናቸው ተናግረዋል። ወታደሩ ለአንድ ዓመት በስልጣን ላይ እንደሚቆይም ገልጿል።

በርካታ ወታደሮች በአገሪቱ ዋና ከተማ ናይፒታው እና በሌላኛዋ ዋነኛ ከተማ ያንጎን ይታያሉ። በርካታ ወታደሮች በተለያዩ ቦታዎች እየሄዱ የሲቪል አስተዳደሩ ሚኒስትሮች የነበሩ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

የሞባይል እና ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም ስልክ በስፋት የተቋረጠባቸው ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሲሆን የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ሥርጭት ለማድረስ እክል እንደገጠመው በመግለፅ ተቋርጧል።

Via BBC , Tikvah

t.me/geradomedia