Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል ምርጫ የሚከናወንበት ሁኔታ...... በትግራይ ክልል አሁን ባለው ሁኔታ ከሌሎች ክ | ገራዶ ሚዲያ

በትግራይ ክልል ምርጫ የሚከናወንበት ሁኔታ......

በትግራይ ክልል አሁን ባለው ሁኔታ ከሌሎች ክልሎች እኩል ምርጫ ሊደረግ እንደማይችል የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ከህዝብ ለተሰበሰቡ ጥያቄዎች በቦርዱ የፌስቡክ ገፅ ላይ በቀጥታ ምላሽ በሰጡበት ወቅት አረጋግጠዋል።

ወ/ሪት ብርቱካን በምላሻቸው፥ "... በክልሉ ያለው ሁኔታ ሲሻሻል በጥቂት የቀናት ልዩነት ከሌሎቹ ክልሎች ከሚደረገው ምርጫ ጋር አንድ ላይ ውጤቱ Merge የሚያደርግበትን ሁኔታና ፓርላማ በሚከፈትበት ጊዜ የሁሉም ውጤት አብሮ የሚቀርብበት ሁኔታን ለማየት ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።

ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ አስፈላጊው ቁሳቁስ መሟላቱን እና ዝግጅት መጠናቀቁን፤ ምርጫው ዘግይቶም ቢካሄድ ከሌሎች ክልሎች ጋር ውጤቱ የሚገለፅበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የተለያዩ አሰራሮች እንደሚኖሩም ወ/ሪት ብርቱካን ተናግረዋል። #Tikvah

t.me/geradomedia