34ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ.....- ጉባኤው ለሁለት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ትላንት ምሽት ተጠናቋል።
- በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ጉባኤው በቪድዮ ኮንፈረንስ ነው የተካሄደው።
- "የአፍሪካን ባህል፣ ኪነት፣ ሙዚቃ ፣ ቋንቋና ትውፊት ይዘን አፍሪካን ወደምንፈልግበት እናደርሳለን" የሚል መሪ ቃል ነበረው።
- የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዜዳንት ፌሌክስ ቺሲኬዲ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
- አዲሱ ሊቀመንበር አዲስ አበባ ተገኘተው የAU ጉባኤ አዳራሽ ውስጥ ከቀድሞ ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዜዳንት ራማፎሳ (እሳቸው ቨርቿል) ሆነው ርክክብ አድርገዋል።
- ከቻድ ሙሳ ፋኪ እንደገና የAU ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተመርጠዋል። ምክትል ኮሚሽነር የሩዋንዳዋ ዶክተር ሞኒክ Nsanzabaganwa ሆነው ተመርጠዋል።
- የአፍሪካ ሰላም ጉዳይ፣ የኢኮኖሚ ውህደት፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር በአፍሪካ ማስፈን ሌሎች አፍሪካን እየተፈታተኑ ያሉ ችግሮችን የሚያነሱ አጀንዳዎች ነበሩ። በዋነኝነት ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መዋጋት፣ ክትባት ለሁሉም ማዳረስ የሚሉት ሃሳቦች ተነስተውበታል።
Via Ambassador Dina Mufti #Tikvah
t.me/geradomedia