🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የነ አቶ ጃዋርና በቀለ ገርባ የረሃብ አድማ.... እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ | ገራዶ ሚዲያ

የነ አቶ ጃዋርና በቀለ ገርባ የረሃብ አድማ....

እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን ጠሃ የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ 12 ቀናት እንደሆናቸው ከOromo Political Prisoners Defense Team የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ቢቢሲ እንዳስነበበው ከሆነ ደግሞ ከአራቱ በተጨማሪም በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር የሚገኙ ተከሳሾች የረሃብ አድማውን ተቀላቅለዋል።

ተከሳሾቹ የአቶ ጃዋር መሐመድ ጠባቂዎች እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ ሲሆኑ አድማውን ከተቀላቀሉ 6 ቀናት አልፏቸዋል።

ይህን ያሳወቁት ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ምስጋኑ ሙለታ ናቸው።

እነ አቶ ጃዋር መሐመድን ትናንት ጠዋት መጎብኘታቸውን የሚያስረዱት ጠበቃው፥ "ትናንት 11ኛ ቀናቸው ነበር። በጣም ተዳክመዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

የአቶ በቀለ ገርባ ባለቤት ወ/ሮ ሃና ረጋሳ ለቢቢሲ፤ እነ አቶ በቀለ አሁንም በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።

የጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ ባለቤት ታደለች መርጋ፥ ባለቤቷ የረሃብ አድማውን መቀላቀሉን እና ለመጠየቅ ይዛለት የምትሄደውን ምግብ አልቀበልም እያላት መሆኑን ገልጻለች።

ጠበቃ አቶ ሙለታ፥ "አንዳንዶቹ በሰው ድጋፍ ነው ከክፍላቸው የሚወጡት። በተለየ ደግሞ ዘግይተው የረሃብ አድማውን የተቀላቀሉት በጣም ከብዷቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

የእነ አቶ ጃዋር ሃኪሞች "ምርመራ ካደረጉላቸው በኋላ ውሃ ካልወሰዱ አንዳንድ የሰውነት አካላቸው ሥራ ሊያቆም እንደሚችል ከነገሯቸው በኋላ ነው በግድ ውሃ እየወሰዱ ያሉት። ምግብ የሚባል ነገር አፋቸው ጋር እየደረሰ አይደለም" ሲሉ አስረድተዋል።

Via BBC & Oromo Political Prisoners Defense Team #tikvah

t.me/geradomedia