🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የኢትዮጵያ እውነት ያሸንፋል!!!! በኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድባችን (#GERD) ዙሪያ ይጠበቅ | ገራዶ ሚዲያ

የኢትዮጵያ እውነት ያሸንፋል!!!!

በኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድባችን (#GERD) ዙሪያ ይጠበቅ የነበረው ክርክር ተካሄዷል:: ሚሊዮኖች በቀጥታ ስርጭት በሚከታተሉት በአልጀዚራ "Scenario" በሚባል ታዋቂ ፕሮግራም ላይ በተካሄደው በዚህ ክርክር ላይ፣ ዛሬም የኢትዮጵያ ሃሳብ አሸናፊ ሆኖ የወጣበት መሆኑ ታውቋል!!!!

በዚህ የክርክር ፕሮግራም ላይ ግብፅም ሱዳንም አሉኝ የሚሏቸውን የፖለቲካ ተንታኞች ያሳተፉ ሲሆን ፕሮግራሙን ለየት የሚያደርገው ደግሞ በቅርቡ ከኢትዮጵያ የተባረረው የኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ተንታኝ እና የጁንታው ወዳጅ የሆነው ዊሊያም ዴቪሰን ተካፋይ የነበረበት ክርክር መሆኑ ነው፡፡

በኛ በኩል ደግሞ የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኝ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር የሆነው ጀግናው ወንድማችን ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ ኢትዮጵያችንን ወክሎ ተሰልፏል!!! ተሟግቷል!!! በብርቱ ተጋድሏል!!!! በጠላት ወገን የቆሙትን ወደረኞቹን ሃቅን ይዞ ተፋልሟል!!!! የኢትዮጵያ አምላክም ረድቶታል!!!! የኢትዮጵያ ሃሳብ አሸናፊ ሆኖ ወጥቷል!!!!

እውነት ያሸንፋል!!!!
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!!!
የህዳሴው ግድብ ዲጂታል ሰራዊት ክብሩልን!!!!
ጀግኖቻችን እንወዳችኃለን!!!! እናከብራችኃለን

የክርክሩን #አማርኛ ትርጉም ቆየት ብለን እናቀርባለን!

Via Dejene Assefa

t.me/geradomedia