🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ዜና እረፍት አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኮቪድ-19 ህይወቱ አለፈ! የዙምራ ፊልም፣ የሰው ለሰው | ገራዶ ሚዲያ

ዜና እረፍት

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኮቪድ-19 ህይወቱ አለፈ!

የዙምራ ፊልም፣ የሰው ለሰው እና የዘመን ድራማ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲና ተዋናይ የነበረው አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኮቪድ-19 ተይዞ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቢቆይም በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ ምክንያት በ50 አመቱ ህይወቱ ማለፉን etv ዘግቧል።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር። ገራዶ ሚዲያ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል፡፡

t.me/geradomedia