Get Mystery Box with random crypto!

ሱዳን ከግድቡ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ እንደሚሰጥ እምነቷ መሆኑን ገለፀ | ገራዶ ሚዲያ

ሱዳን ከግድቡ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ እንደሚሰጥ እምነቷ መሆኑን ገለፀች!

ሱዳን ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ውጤታማና ፈጣን መፍትሄ ላይ እንደሚደረስ እምነቷ መሆኑንን አስታውቃለች። ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መሪ ቃል የሶስትዮሽ ድርድሩ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላት ነው ሱዳን የገለፀችው።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ወሳኙን እና አዲስ ሃሳብና አሰራር የሚመጣበትን የአፍሪካ ህብረትን እንደሚያደንቅ መግለፁን ሱና ዘግቧል። ከዚህ ጋር ተያይዞም ሱዳን አቋሟን ለማስረዳት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የሚመራ ልዑክ ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ እንደምትልክ ገልጻለች።

Via FBC

t.me/geradomedia