Get Mystery Box with random crypto!

'ደም አፋሳሽ ድርጊቶችን የሚደግፍ ሰው ሰይጣናዊ መንፈስ ያለበት ነው' - ሼህ መሀመድ ሲራጅ | ገራዶ ሚዲያ

"ደም አፋሳሽ ድርጊቶችን የሚደግፍ ሰው ሰይጣናዊ መንፈስ ያለበት ነው" - ሼህ መሀመድ ሲራጅ

ደም አፋሳሽ የሆኑ ድርጊቶችን የሚደግፍ ሰው ሰይጣናዊ መንፈስ ያለበት እንደሆነ እና በአሁኑ ወቅትም በአገሪቱ የሚታዩ ነገሮች ደስ እንደማያሰ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ዑለማ ምክር ቤት አባልና የሰላም ዘርፍ ሃላፊ ሼህ መሀመድ ሲራጅ ገለፁ። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የሚታዩ ነገሮች ደስ እንደማያሰኙ አስታወቁ።

ሼህ መሀመድ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ የፈጣሪን ሕግና መመሪያን የሚያከብር ሰው እርስ በእርስ በሚያጋጩ፣ በሚያጣሉ፣ ደም በሚያፋስሱና በሚያጨፋጭፉ ድርጊቶች ላይ አይተባበርም። ድርጊቱን የሚፈጽሙ ሰዎች ዛሬ በሚሰሩት ሥራ ነገ መፀፀታቸው አይቀርምና ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው።

ሌሎችን የሚያሰቃይ፣ ሕይወታቸውን የሚቀጥፍ፣ ደማቸውን የሚያፈስ፣ ንብረታቸውን የሚያጠፋ፣ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ከሚበትን አቋምና አስተሳሰብ መውጣት ይገባቸዋል ያሉት ሼህ መሀመድ፣ እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጽም በዚች ምድር ላይ ተረጋግቶ አይኖርም። ቆም ብሎ ማስተዋል እንዳለበት አመልክተዋል።

"ተንኮል፣ ምቀኝነትና ሰዎች ላይ ጥቃት ማድረስ አረመኔያዊነት ተግባር ነው። ድርጊቱን የሚፈጽምም በምድር ላይ በደስታ አይኖርም፣ ቀጣይ ህይወቱም ሰቆቃ፣ መከራና ችግር ይገጥመዋል" ብለዋል።

ድርጊቱን የሚፈጽመው በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹና በወገኖቹ ላይ ነው። ፈጣሪ የተረጋጋ መንፈስ አይሰጠውም። ማንም ሰው እንዲህ አይነት ድርጊት በእናቱ፣ በልጁ፣ በአባቱ ላይ ቢደረግበት አይወድም፤ በእራሱ ላይ ሊደረግ የማይወደውን ነገር በሌሎች ላይ ማድረግ እንደሌለበት አስታውቀዋል። #EPA

t.me/geradomedia