Get Mystery Box with random crypto!

#ኢዜማ #መግለጫ በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አዘጋጅቶታል የተባለውና “የሃገሪቷ | ገራዶ ሚዲያ

#ኢዜማ #መግለጫ

በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አዘጋጅቶታል የተባለውና “የሃገሪቷ ወቅታዊ የደህንነት ስጋት ትንተና” የሚል ርእስ ያለው የኢዜማ ሚስጥራዊ ሰነድ ነው ተብሎ ከትላንት ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ነው። የነጻነትና እኩልነት ፓርቲም (ነእፓ) በዚሁ ሰነድ ላይ ስሜ አሉታዊ በሆነ መንገድ በመጠቀሱ ማብራሪያ ይሰጠኝ ሲል ለኢዜማ በደብዳቤ ጠይቆ ነበር።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ህዝብ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ከትላንት ጀምሮ ሲዘዋወር የነበረውን ሰነድ "ኢዜማን የማያወክል እና ኢዜማ የማያዉቀዉ" ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

t.me/geradomedia