Get Mystery Box with random crypto!

በአስዋን ግድብ አቅራቢያ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ...... ግብፅ 37% የሀገሪቱን የኤሌክትሪ | ገራዶ ሚዲያ

በአስዋን ግድብ አቅራቢያ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ......

ግብፅ 37% የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ሀይል በሚሸፍንላት ሽማግሌው የአስዋን ግድብ ያረፈበት ቦታ ላይ በሬክተር ስኬል 3.1 የሆነ “የመሬት መንቀጥቀጥ” እንዳጋጠመ Egypt Independent ዘግቧል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአካባቢው ሰዎች ስሜቱን ያስተዋሉት ሲሆን፣ ምንም አይነት ጉዳት አላደረሰም ተብሏል። ነገር ግን ከዚህ በፊት ግብፃዊያን በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት እኤአ አቆጣጣር በ1903 - 10 ሺህ ሰዎች፣ በ1985 - 5 ሰዎች፣ በ1992 - 541 ሰዎች ሲሞቱ፤ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ካይሮ ደግሞ
398 ፎቆችንና 8 ሺህ ቪላ ቤቶችን ማፍረሱን የግብፅ የመሬት መንቀጥቀጥ ታሪክ ይናገራል!

በተቃራኒው እነሱ "የህዳሴ ግድቡ የሚሰራበት ቦታ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከትላል! ይሄም የወደፊት የሱዳን ስጋት ነው!" እያሉ ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ እንድታምፅ ይገፋፉ ነበር !

Via ሱሌማን አብደላ

t.me/geradomedia