Get Mystery Box with random crypto!

#ለጥንቃቄ በሚቀጥሉት 5 ቀናት በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እን | ገራዶ ሚዲያ

#ለጥንቃቄ

በሚቀጥሉት 5 ቀናት በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ አሳሰበ!

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም እንዳሉት፥ ባለፉት ሁለት ወራት የፓስፊክ ውቂያኖስ ምስራቃዊና ማዕከላዊ የውሃ አካል ከመደበኛ በታች የመቀዝቀዝ ሁኔታ መስተዋሉን ተከትሎ የዘንድሮው የበልግ ወቅት መቆራረጥ ታይቶበታል፡፡

ከተያዘው ወር ጀምሮ ግን ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ሁኔታ እየተመለሰ መሆኑን የአለም አቀፍ የትንበያ ማዕከላት ማሳወቃቸውን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

አክለውም በኦሮሚያ ክልል በሁሉም የወለጋ ዞኖች፣ ጅማ፣ ኢሊባቡር፣ የሸዋ ዞኖች፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂ እንዲሁም የሱማሌ ክልል፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና የደቡብ ወሎ ዞኖች፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ደቡብ ጎንደር፤ የሲዳማ ክልልና አንዳንድ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል አቶ አህመዲን ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪ በሚቀጥሉት 5 ቀናት ውስጥ የደቡብ ምዕራብ እና የደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖራቸው እንደሚችልም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

[አሐዱ ራዲዮ]

t.me/geradomedia