Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር... በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ | ገራዶ ሚዲያ

አዲሱ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር...

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ተኮላ አይፎክሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን እንዲመሩ መሾማቸው ታወቀ።

አቶ ተኮላ ከትናንት ሚያዚያ 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው መመደባቸው ታውቋል። የቀድሞው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ከሁለት ዓመታት በላይ በኃላፊነቱ ሲሰሩ ቆይተዋል።

በቅርቡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው አቶ ተኮላ በአቶ አበረ አዳሙ ምትክ ወደ ኃላፊነት የመጡት።

ከ3 ዓመት በፊት በፌደራል ፖሊስ ውስጥ በኃላፊነት ከመመደባቸው አስቀድሞ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ ቦታዎች አገልግለዋል። በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ አዛዥ፣ የአምባሰል ወረዳ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ሠርተዋል። #BBC

t.me/geradomedia