Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ ሁኔታ ስለ አጣዬ፣ ከሚሴ፣ ሸዋ ሮቢት....... በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብ | ገራዶ ሚዲያ

ወቅታዊ ሁኔታ ስለ አጣዬ፣ ከሚሴ፣ ሸዋ ሮቢት.......

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በቅርቡ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ተረጋግቶ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት አስታወቀ። አጥፊዎችን የመለየትና በህግ ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎችም እየተከናወኑ ነው ብሏል።

የኮማንድ ፖስቱ አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አቢቼ ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ ኮማንድ ፖስቱ ግዳጅ ከተሰጠው ጀምሮ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ግጭትና ጸብ አጫሪነትን እንዲሁም መንገድ መዝጋትን በማስቆም የተቋረጡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ሥራዎች እንዲጀመሩ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው የመመለስና አጥፊዎችን ለይቶ ለህግ እንዲቀርቡ የማድረግ ሥራም ከኮማንድ ፖስቱ ተግባራት መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በእነዚህ ላይ አተኩሮ በመሰራቱም በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ግጭትና የወንጀል ድርጊቶች መቆማቸውን ነው የተናገሩት።

አካባቢው የተረጋጋ እንቅስቃሴ እየታየበት በመሆኑ ተቋርጠው የነበሩ የስልክ፣ የውሃና የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች እንድሁም የትራንስፖርትና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።

አስተባባሪው እንዳሉት አጥፊዎችን በፍጥነት የመለየትና በህግ ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ። ህዝቡ ሰላም ፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ ከመንግስት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ችግር የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና የመንግስት መዋቅር እጅ እንዳለበት መታወቁንና በቀጣይ በማስረጃ የተደገፉ መረጃዎች የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራ አስተባባሪው ገልጸዋል። #ENA

t.me/geradomedia