Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን ታጣቂዎች ጥቃት......... የሱዳን ታጣቂዎች ዛሬ በምዕራብ ጎንደር ዞን መንዶካ ልዩ ስ | ገራዶ ሚዲያ

የሱዳን ታጣቂዎች ጥቃት.........

የሱዳን ታጣቂዎች ዛሬ በምዕራብ ጎንደር ዞን መንዶካ ልዩ ስሙ እንዲብሎ በተባለ ቦታ ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋት 4 ሰዓት ተኩስ ከፍተው የግብርና ባለሀብቶችን ካምፕ ማቃጠላቸውን አንድ የአካባቢው ነዋሪ ገልፀዋል። እነዚህ ኃይሎች ከርቀት ከፍተኛ ድምፅ ያለው መሳሪያ ሲተኩሱ እንደነበር ነው ነዋሪው የገለፁት፡፡

መንዶካ ከሱዳን ደንበር 70 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአካባቢ ሚሊሺያና ሌሎችም የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ የሱዳን ኃይሎች ተመልሰዋል ሲሉ ነዋሪው ገልጸዋል።

የመተማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፋንታሁን ኪሮስ “መከላከያም፣ ፀረ ሽምቅም፣ ሚሊሺያም ወደ ቦታው ልከናል፤ አሁን ተረጋግቷል፣»ሲሉ በስልክ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ከጥቅምት መጨረሻ ጀምሮ በአንድንድ የምዕራብ አማራ ወረዳዎች ዘልቀው በመግባት የባለሀብቶችን ንብረት የሚያወድሙት የሚዘርፉትና የሚያቃጥሉት የሱዳን ታጣቂዎች አሁንም ከኢትዮጵያ ግዛት እንዳልወጡ የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ አስታውቋል።

t.me/geradomedia