Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ያለዉ ቀዉስ 5ሺ ህጻናትን ከወላጆቻቸዉ እንደነጠለ ሴቭ ዘ-ችልድረን አስታወቀ! ዓለም አ | ገራዶ ሚዲያ

በትግራይ ያለዉ ቀዉስ 5ሺ ህጻናትን ከወላጆቻቸዉ እንደነጠለ ሴቭ ዘ-ችልድረን አስታወቀ!

ዓለም አቀፉ የረድኤት ተቋም ሴቭ ዘ-ችልድረን እንዳስታወቀዉ በሰሜን ኢትዮጲያ ትግራይ ክልል ያለዉ ቀዉስ 5ሺ ህጻናትን ከወላጆቻቸዉ እንደነጠለ ይፋ አድርጓል፡፡ በርካታ ህጻናት ከቤተሰቦቻቸዉ ከተነጠሉ በኃላ በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አልያም ይፋዊ ባልሆነ ስፍራ ተሸሽገዉ ይገኛሉ፡፡

ዓለም አቀፉ የረድኤት ተቋም ሴቭ ዘ-ችልድረን እንደሚለዉ እነዚሁ ህጻናት ለረሃብ፣ ለወሲባዊ ጥቃትና ለአካላዊ ጉዳት ሰለባ ስለመሆናቸዉ በሪፖርቱ ዉስጥ ተካቷል፡፡ የረድኤት ተቋማት ወደ ተጎጂዎች ስፍራ ለመድረስ አሁንም እንዳልተቻላቸዉ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

#ትኩረት

t.me/geradomedia