🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አብሪ ማይንድስ እና ኮሳፕ በጋራ ለመስራት የሚያስችል  የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። ኮሳፕ በስ | Hana Hailu

አብሪ ማይንድስ እና ኮሳፕ በጋራ ለመስራት የሚያስችል  የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ኮሳፕ በስሩ ተጠቃሚ የሆኑትን ከ250 ሺ በላይ ሴቶች ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የአብሪ ማይንድስ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ሀና ሀይሉን አምባሳደር አድርጎ ለቀጣይ አንድ አመታት ሾሟል።

ኮሳፕ በኢትዮጲያ ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ የራስ አገዝ ቡድኖችን ያቋቋመ ሲሆን በአጠቃላይ በእነዚህ ቡድኖች ከ250ሺ በላይ ሴቶች እና አናቶችን በስሩ በአባልነት ይዟል።

እነዚህ ሴቶች ባዳበሩት የቁጠባ ባህል ከ270,922,076 ብር በላይ ካፒታል መጠን በማፍራት በሀገራችን ዘርፈ ብዙ ለውጥ እያመጡ እንደሆነ ተናግረዋል።

የኮሳፕ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አካሉ የእነዚህን ሴቶች ተሰሚነት እንዲጨምር እንዲሁም ሴቶች  በይበልጥ እንዲሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ከአብሪ ማይንድስ ጋር ለመስራት እቅድ እንደያዙ አሳውቀዋል።

በቀጣይ 3 ወራት ከኮሳፕ ጋር በመተባበር 50ሺ ወጣት እና ከስደት ተመላሽ ሴቶችን ሊያዳርስ የሚችል ስራ በመስራት ንቅናቄ እቅዳቸው መሆኑን አዲሷ አምባሳደር ወ/ሪት ሀና ሀይሉ ገልጻለች። እነዚህ ሴቶች እና እናቶች ጥቅም የድርሻቸውን እንደምትወጣ ገልጻለች።

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot