Get Mystery Box with random crypto!

ሕጋዊ መከላከል • የራስን ወይም የሌላውን ሰው መብት ህገ ወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ | Corporate Lawyer

ሕጋዊ መከላከል
• የራስን ወይም የሌላውን ሰው መብት ህገ ወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ ህገወጥ ጥቃት ለማዳን ጥቃቱ እንዳይደርስ ለማድረግ ሌላ መንገድ ሳይኖር ከሁኔታው መጠን ባለማለፍ የተፈጸመ ድርጊት::
ህጋዊ መከላከል በወንጀል የማያስቀጣው የራስን ወይም የሌላውን ሰው መብት ህገ ወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ ህገወጥ ጥቃት ለማዳን ጥቃቱ እንዳይደርስ ለማድረግ ሌላ መንገድ ሳይኖር ከሁኔታው መጠን ባለማለፍ የተፈጸመ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ. ሪብሊክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 78 ይዘትና መንፈስ የምንረዳው ጉዳይ ነው፡፡ ሕጋዊ መከላከል የወንጀል ተጠያቂነትን የማያስከትለው ተመጣጣኝ የሆነ ዘዴ ወይም መሳሪያ በመጠቀም በቅርብ መድረሱ የማይቀረውን ህገ ወጥ የሆነ ጥቃት ለመከላከል አስፈላጊ የሆነ ድርጊት መፈፀም ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ. ሪብሊክ የወንጀል ህግ አንቀፅ 78 እነ 79 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ በግልጽ ያሳያል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 86570 ቅጽ 15፣ ወ/ህ/ቁ. 78፣ 79
ህጋዊ መከላከልን ከመጠን ማሳለፍ የወንጀሉ ማቋቋሚያ በሆነ ጊዜ እንደ ቅጣት ማቅለያ ምክንያት አይወሰድም፡፡ ህጋዊ መከላከል የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ስለመሆኑ የወ/ሕጉ አንቀጽ 79/1/ ይገልፃል፡፡ በወ/ሕጉ አንቀጽ 541/ሀ/ ሥር ከተመለከቱት የድንጌጋው ማቋቋምያ ምክንያቶች አንዱ ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሳለፍ የተፈፀመ የነፍስ ግድያ ወንጀል እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ የወ/ሕጉ አንቀጽ 79/1/ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አድርጎ በገለፀው አኳኋን አንቀጽ 541/ሀ/ ሁለተኛው ሀረግ ደግሞ ወንጀሉን ለማቋቋም እንደሚችል ደንግጓል፡፡ እንዲህ አይነት ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ በወ/ሕጉ አንቀጽ 82/2/ እንደተደነገገው ድርጊቱን ለማቋቋም የተደነገገው ልዩ ክፍል ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 57446 ቅጽ 12፣ ወ/ህ/ቁ. 79፣ 82(2)፣ 84(2)
Source :-Amharic Legal Glossary,




@Henoktayelawoffice