Get Mystery Box with random crypto!

በንግድ ሕግ ቁ. 674/1/ ድንጋጌ መሰረት በኢንሹራንስ ውል ላይ ተመስርቶ የሚቀርብ ማንኛውም ክስ | Corporate Lawyer

በንግድ ሕግ ቁ. 674/1/ ድንጋጌ መሰረት በኢንሹራንስ ውል ላይ ተመስርቶ የሚቀርብ ማንኛውም ክስ ጥያቄውን ለማቅረብ የሚያስችለው ምክንያት በተከሰተ ወይም ጥቅም ያላቸው ወገኖች ጉዳዩን ካወቁበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመት ጊዜውስጥ መቅረብ አለበት፡፡ የይርጋ ጊዜውን ለመወሰን የፍትሐብሔር ሕግ ቁ. 1677 እና 1845 በኢንሹራንስ ጉዳይ ላይ አግባብነት የላቸውም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 46778 ቅጽ 10፣ ን/ህ/ቁ. 674/1/፣ ፍ/ህ/ቁ. 1677፣ 1845

ጉዳት የደረሰው በመድን ዋስትና ውል ባልተሸፈነ ሁኔታ ነው በሚል ምክንያት የኢንሹራንስ ድርጅት የከፈለው ካሳ እንዲመለስለት የሚያቀርበው ክስ ሁኔታውን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ይታገዳል፡፡

በተሸሸገ ወይም በሐሰት ቃል የቀረበ ጉዳይ ያጋጠመ ሲሆን የይርጋው ዘመን የሚታሰበው ኢንሹራንስ ሰጪው የተሸሸገውን ወይም በሐሰት የቀረበውን ቃል ካወቀበት ቀን ጀምሮ

እንደሆነ በንግድ ሕግ ቁ. 674(2) ተደንግጓል፡፡ የይርጋው ዘመን ሁለት ዓመት እንደሆነም በዚሁ ቁጥር ንኡስ ቁ (1) ተመልክቷል፡፡

ሰ/መ/ቁ 42309 ቅጽ 9፣[11] ን/ህ/ቁ. 674/1/

6. የመድን ጥቅም

የመድን ጥቅም /insurable interest/ ያለው ሰው ሲባል በደረሰው አደጋ ወይም ጉዳት በትክክል የተጎዳ ወይም ሊጎዳ የሚችል ሰው ማለት ነው፡፡

መድን ሰጪው ካሣ የሚቀበለው ጉዳት በደረሰበት ወቅት ጉዳት በደረሰበት ንብረት ወይም እቃ ላይ የመድን ጥቅም ያለው ሰው ሲሆን የመድን ጥቅም የሌለው ሰው ካሣ ለመጠየቅ የሚያስችለው የሕግ መሰረት የለውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 47004 ቅጽ 13[12] Abrham Yohannes