Get Mystery Box with random crypto!

የአካባቢያዊ ማስረጃ ምዘና ---------------- የሰ/መ/ቁ109441፡-የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ | Corporate Lawyer

የአካባቢያዊ ማስረጃ ምዘና
----------------
የሰ/መ/ቁ109441፡-የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ ወንጀልን የፈፀመው ተከሳሽ መሆኑንና ከተከሳሽ
ውጭ ሌላ ሰው ወንጀሉን ሊፈፅመው አይችልም ከሚል መደምደሚያ ላይ ለመድረስ በቂና
አሳማኝ በሆነ ሁኔታ የሚያስረዳ ሆኖ ሲገኝ የአስረጅነት ብቃት ያለው ማስረጃ ተደርጎ
እንደሚወሰድ የማስረጃ ብቃት መስፈርትና የማስረጃ አመዛዘን መርሆች ያሳያሉ፡፡የአካባቢ
ሁኔታ ማስረጃ አንድን የተፈፀመ ወንጀል ለማስረዳት የአስረጅነት ብቃት ያለው ማስረጃ
የሚሆነው ወንጀል ከመፈፀሙ በፉት እና ወንጀሉ ከተፈፀመ በኃላ ስላለው ሁኔታ የተረጋገጡት
ፍሬ ነገሮች (የአካባቢ ሁኔታዎች) ተከሳሽ ወንጀሉን ፈፅሞታል ከሚል እርግጠኛ መደምደሚያ
መድረስ የሚያስችል ይዘትና ባህሪ ያላቸው ሲሆን: የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃዎች ተያያዣነት
ያላቸውና ክፍተት የሌለባቸው ሲሆኑ፤ የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃዎች የተከሳሹን
ወንጀል መስራት የሚያረጋግጡ እንጅ በተቃራኒው ተከሳሹ ንፁህ ነው፣ወንጀሉን አልፈፀመም
ወደሚለው ሎጂካል መደምደሚያ የማይወስዱ ሲሆንና የቀረቡት የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃዎች
በማናቸውም የሞራልና የህሊና መመዘኛ ወንጀሉ በተከሳሽ ሳይሆን በሌላ ሰው የመፈጸም
እድልና አጋጣሚ የሌለ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማስረዳት የሚችሉ ሆነው ሲገኙ እንደሆነ
ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ህግ መርሆች ያሳያሉ፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 27(2) የሠጠውን የተከሳሽነት ቃል ተከሳሽ ላቀረበው
ማስረጃ ማስተባበያነት ከተጠቀመበት በዚህ ቃል ውስጥ ተከሳሽን የሚጠቅም ነገር ካለ የተከሳሽን
ቃል ከእነሙሉ ይዘቱ ሊቀበል ይገባል እንጅ ተከሳሽን ጥፋተኛ የሚያስብለውን የቃሉን ክፍል ብቻ
ወስዶ ከጥፋቱ ነፃ የሚያደርገውን ክፍል መተው መሠረታዊ የማስረጃ ምዘና መርህን
ያልተከተለ ነው፡፡
በመሆኑም በተሠሙት የአካባቢ ምስክሮች ወንጀሉን ከተከሳሹ ውጪ ሌላ ሰው ሊፈፅመው
የሚችልበት እድል አለመኖሩን በሚያረጋግጥ መልኩ ካላስረዱ ተከሳሽ ተከላከል ሊባል
አይገባም፡፡ቅጽ/19
(ከተጠቃለሉ የሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች ከቅፅ1-23 መፅሀፍ የተወሰደ)
@Henoktayelawoffice