Get Mystery Box with random crypto!

ጭብጥ =============== • ተከራካሪ ወገኖች የተለያዩበት የህግ ወይም የፍሬ ነገር ጉዳይ | Corporate Lawyer

ጭብጥ
===============
• ተከራካሪ ወገኖች የተለያዩበት የህግ ወይም የፍሬ ነገር ጉዳይ

ማንኛውም ፍርድ ቤት ባለጉዳዮችን ማከራከር የሚገባው የተለያዩበት የሕግ ወይም የፍሬ ነገር አግባብ ምን እንደሆነ አረጋግጦ ለጉዳዩ ትክክለኛ ጭብጥ በመያዝ ስለመሆኑ፣ የነገር ጭብጥ የሚመሰረተው አንደኛው ተከራካሪ ወገን ያመነውን የሕግ ወይም የነገር አግባብ ሌላኛው ተከራካሪ ወገን በማስተባበል የካደ በሆነ ጊዜ ስለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ጭብጥን ለመመስረት የሚችለውም ከግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር እና ማስረጃ እንዲሁም በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 241 መሰረት በሚደረግ ምርመራ በተከራካካሪ ወገኖች የሚሰጠውን መልስ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ የጭብጥ አመሰራረትን በሚደነግጉት ከቁጥር 246 እስከ 248 በተመለከቱት የስነ ስርዓት ሕጉ ድንገጌዎች እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ በክርክሩ የተያዘው ጭብጥ ምን እንደሆነ እና ጭብጡ በአንድ ወይም በሌላ አግባብ የተወሰነበትን ምክንያት በውሳኔው ላይ መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ የፍርድ አጻጻፍን በሚመለከተው በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 182(1) ስር በአስገዳጅነት ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 105869 ቅጽ 18፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 182(1)፣ 241፣ 246-248
@Henoktayelawoffice join