Get Mystery Box with random crypto!

አዎንታዊ አስተሳሰብ አዎንታዊ አስተሳሰብ በህይወት የሚገጥሙንን ወይም ሊገጥሙን የሚችሉ ጥሩ ያልሆ | 21St C. Soul

አዎንታዊ አስተሳሰብ

አዎንታዊ አስተሳሰብ በህይወት የሚገጥሙንን ወይም ሊገጥሙን የሚችሉ ጥሩ ያልሆኑ መጥፎ ነገሮችን አለማሰብ ማለት አይደለም። አዎንታዊ አስተሳሰብ የምንለው በአዕምሮ እና በስሜት ላይ የተደገፉ ሀሳቦችን ጥሩ ወይም መልካም ዉጤት ላይ የሚያተኩር አስተሳሰብ ሲሆን፤ ያሰብናቸዉ ዕቅዶችም ሳይሳኩ ሲቀሩ ተስፋ አለመቁረጥ ማለትነው ።

በህይወታችን ወይም በነገሮቻችን ላይ የሚኖረን አዎንታዊ አስተሳሰብ የትኛውንም አይነት አሉታዊ የሆነ አዕምሮአችንን እና ስሜታችንን (mood) ሊረብሹ ከሚችሉ ተፅዕኖዎች ነፃ እንድሆን ያደረጋል።

አዎንታዊ አስተሳሰብ ከራሳችን ጋር ከሚኖረን ንግግር ይጀምራል። ከራሳችን ጋር የሚኖረን ንግግር ደግሞ በአዕምሮአችን ዉስጥ የምሄዱ እና የምመጡ የማያቋርጥ ያልተነገሩ ሀሳቦችን የያዘነዉ። እነዚህ ሀሳቦች ደግሞ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ሊሆኑ ይችላሉ።
አብዛኛውን ጊዜ ሀሳባችን መልካም ወይም አዎንታዊ ከሆነ ለራሳችንም ሆነ ለሰዎች አልፎም
ለሀገራችን ብሩህ አመለካከት ይኖረናል።

የስነልቦና ባለሙያዎች አዎንታዊ አስተሳሰብ በጤና ላይ እጅግ በጣም ጠቃሚ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይገልፃሉ። በጤና ላይ ከሚኖራቸው ጠቀሜታ መካከል፦

ጭንቀትን እና ድብርትን ይቀንሳል፣ በአተነፋፈስ ችግር እና በካንሰር በሽታ የሚመጣ ሞትን ይቀነሳል እንዲሁም በችግር እና በውጥረት ጊዜ የመቋቋም ክህሎታችንን ያሻሽላል።

ታዲያ እንዴት ነዉ አዎንታዊ አስተሳሰብ ሊኖረን የሚችለው ?

አዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲኖረን የሚያደርጉ የተለያዩ መንገዶች አሉ።
ከነዚህም መካከል አንዱ መንገድ ቀላል የሆነ ደንብ በመከተል መጀመር እንችላለን።
"ለሌሎ ችየማትናገረውን ለራስህ አትናገረው" ይሄ ማለት ቀደም ብሎ እንደተገለፀው ከራሳችን ጋር የሚኖረን ንንግግር እንድናስተካክለው ይረዳናል።

አዕምሮአችንን በሚያበረታታ እና በሚያነሳሱ ሀሳብ መሙላት እንችላለን፡፡ ሆኖም ወደ አዕምሮአችን አሉታዊ ሀሳቦች መምጣታቸው አይቀሬ ነው፡፡ እነዚህን አሉታዊ ሀሳቦች ደግሞ መልካም እና ብሩህ በሆኑ ሀሳቦች እየተካን አዎንታዊ አስተሳሰብን መያዝ እንችላለን።

ኢምፓክት ኢትዮጵያ | ሐምሌ 19 / 2014