🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት ክፍያ ውጭ ማንኛውንም ወጭ መጠየቅ አይችሉም - የአዲስ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት ክፍያ ውጭ ማንኛውንም ወጭ መጠየቅ አይችሉም - የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን
********

የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት ክፍያ ውጭ ማንኛውንም ወጭ ከተማሪ ወላጆች መጠየቅ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በከተማዋ ለቀጣይ የትምህርት ዘመን የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ 1ሺህ253 የግል ት/ቤቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኘው ገብሩ ገልጸዋል።

የግል ትምህርት ቤቶች ዋጋ የሚጨምሩባቸው ምክንያቶች ግብዓቶችን ለማሟላት፣ ለአስተዳደራዊ ወጭዎች እና የትምህርት ጥራትን አስጠብቆ ለማስቀጠል ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውም ተገልጿል።

የዋጋ ጭማሪው ተግባራዊ የሚሆነው ወላጆችና ትምህርት ቤቶች ተወያይተው ሲስማሙ መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል። የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot