Get Mystery Box with random crypto!

CAUTION 'ትምህርት ቤቶች ዳግም ሊዘጉ የሚችሉበት እድል አለ' - የአማራ ክልል ትምህርት | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

CAUTION

"ትምህርት ቤቶች ዳግም ሊዘጉ የሚችሉበት እድል አለ" - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ተግባራዊ ባለመደረጋቸው ትምህርት ቤቶች ዳግም ሊዘጉ የሚችሉበት እድል መኖሩን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ትምህርት ቢሮው ይህን ያሳወቀው በባህር ዳር ከተማ "እንድናገለግሎ ማስክዎን ያድርጉ" የሚል ንቅናቄ በተጀመረበት ወቅት ነው።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተገቢው ጥንቃቄ እየተደረገ ትምህርት እንዲቀጠሎ ተደርጎ መከፈታቸው ይታወሳል።

ምንም እንኳን ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱም በኮሮና ቫይረስ መከላከያ ላይ ያለው አተገባበር በታሰበው መልኩ እየሄደ አይደለም ተብሏል።

ተማሪዎች ትምህርት ቤት ዳግም የተከፈተ ሰሞን ጥሩ ጥንቃቄ ያደረጉ የነበር ሲሆን አሁን ላይ ትኩረት እያጡ መከላከያውም እየተረሳ መሆኑ ተገልጿል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ ፥ አሁን እየታየ ያለው መዘናጋት እና ግዴለሽነቱ ካልቆመ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው ሊዘጉ እንደሚችሉ አሳስበዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለው ፥ በክልሉ ውስጥ ያሉ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያን ተግባራዊ በማድረግ ሊመጣ እና ሊያጋጥም ከሚችለው አደጋ እራስን መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

AMMA/EPA/ENA

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT