Get Mystery Box with random crypto!

ከሚስት ሀቆች ❹ ባሏ ከእሳት ሊጠብቃት (يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُو | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

ከሚስት ሀቆች

❹ ባሏ ከእሳት ሊጠብቃት

(يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنْفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا) [التحريم:6].
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡" ተህሪም 6
 
እንደዚሁም በሰላት ሊያዛት

(وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصْطَبِرْ عَلَيْهَا) [طه:132]
"ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤(ጽና)፡፡ " ጣሃ 132

➬ይህም ማለት ዲናዊ እውቀትን ሊያስተምራት በመልካም ሊያዛት ከመጥፎ ሊከለክላት ሲሆን፤ባጭሩ በአኼራ ከጀሀነም እሳት ተጠብቃ ጀነትን የምትወርስበትን መንገድ ያመቻችላታል ።

ወንድ (ባል)የቤተሰቡ አርዓያ እንደመሆኑ በሁሉም ሁኔታው ከቤተሰቡ አባላት የተሻለ ሊሆን ይገባል።

➬ ወንዱ በተግባር ወይም በእውቀት ከዲን የራቀ ሲሆን ቤተሰብ ብሎም ትውልድ እንዲበላሽ ምክንያት ይሆናል።

ሰዎችን ከምንቀርፅበት አደገኛው መንገድ መጥፎ አርዐያነት ነው።

➬ይህን በተመለከተ ፉደይል ኢብን ዒያድ እንዲህ ይላል፦ማሊክ ኢብኑ ዲናር ሰላቱን ሳያስተካክል የሚሰግድ ሰው ይመለከትና "ለቤተሰቦቹ አዘንኩላቸው" ይላል። "እሱ ሰላቱን ያበላሻል አንተ ለቤተሰቦቹ ታዝናለህ" አሉት።
ማሊክም "እሱ ትልቃቸው ነው ከሱ ነው የሚማሩት" ብሎ መለሰላቸው።

ወንዱ የአላህን ድንበር የሚያስጠብቅ ሳይሆን እራሱ ድንበር የሚተላለፍ፣ በቤቱ አዛዥ መሆኑ ቀርቶ ታዛዥ ሲሆን፣እሱን የሚከተሉት ሳይሆን ተከታይ መሆኑ ደግሞ ሌላው ሙሲባ ነው።
•┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈•

ያ አላህ! ቤተሰብ ይስተካከል ዘንድ የቤተሰብ ሀላፊዎችን አስተካክልልን።

@nesiha_ouserya
#ትዳር #የሚስት ሀቅ