Get Mystery Box with random crypto!

በሩን በማንኳኳት ላይ ታገሱ ፉደይል ኢብን ኢያድ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል፦ ትእግስት | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

በሩን በማንኳኳት ላይ ታገሱ

ፉደይል ኢብን ኢያድ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል፦

ትእግስትን ከህጻን ልጅ ተማርኩኝ

አንድ ቀን ወደ መስድጅ እየሄድኩ አንዲት እናት ቤቷ ሆና ልጇን ትገርፋለች ልጁም እየጮሀ በሩን ከፍቶ ሮጠ እናቱም በሩን ዘጋችበት ።

ከመስጅድ ስመለስ ልጁ ካለቀሰ በኋላ በሚያሳዝን ሁኔታ የቤቱ መቃን ስር ተኝቶ አገኘሁት እናቱም ልብዋ ራራና በሩን ከፈተችለት።

ፉደይልም ጺሙ በእንባ እስከሚርስ ድረስ አለቀሰ።
እንዲህም አለ

ሱብሃነላህ! ባርያው በአላህ عز وجل በር (በማንኳኳት) ቢታገስ አላህ በሩን ይከፍትለታል ።

አቡ ደርዳእ رضي الله عنه እንዲህ አለ፦
በዱአ ጠንክሩ እነሆ በሩን ማንኳኳት የሚያበዛ ሰው ሊከፈትለት ይቀርባል።
...
مصنف ابن أبـﮯ شيبة【 ٦/٢ 】

•┈┈•◈◉❒
#መልዕክት #ዱዓ
@nesiha_ouserya