Get Mystery Box with random crypto!

ነገ የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን ማሟያ ነው! በሁሉም የሳውዲ አካባቢዎች ጨረቃ አልታየችም። ቅርበት | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

ነገ የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን ማሟያ ነው!

በሁሉም የሳውዲ አካባቢዎች ጨረቃ አልታየችም። ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳደረሱን በተሚዝ አካባቢ ያለው የጨረቃ መጠባበቂያ ማእከል ውጤት ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ሆኖም ጨረቃ አልታየችም። በመሆኑም ነገ ሰኞ ሚያዝያ 4/2013 የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን የመጨረሻ ቀን ይሆናል። ማክሰኞ ረመዳን 1 ይሆናል። ከሳውዲ ከፍተኛ ፍርድቤት ይፋ መግለጫ በመጠበቅ ላይ ነው።
ነሲሓ ቲቪ መላውን ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያለ አላህ ተውበትና መልካም ስራን እንዲያገራልን እንለምነዋለን። ረመዳን ሙባረክ!!


ነሲሓ ቲቪ
@nesihatv