Get Mystery Box with random crypto!

በጂቡቲ ከተማ በአፋር እና በሶማሌ ተወላጆች መካከል ግጭት ተከስቶ ነበር ተባለ! በጂቡቲ ዋና ከተ | Crazy jocks 😜😂

በጂቡቲ ከተማ በአፋር እና በሶማሌ ተወላጆች መካከል ግጭት ተከስቶ ነበር ተባለ!

በጂቡቲ ዋና ከተማ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በአፋር እና በሶማሌ ተወላጆች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ እና ንብረት መውደሙ ተገለጸ።የጂቡቲ መንግሥት በዋና ከተማዋ ጂቡቲ በአፋር እና በሶማሌ ተወላጆች መካከል የተነሳውን ግጭት አውግዟል።በግጭቱ ሕይወታቸው ያለፉ ዜጎች ምን ያህል እንደሆኑ እስካሁን ድረስ ያልታወቀ ቢሆንም ንጹሀን ዜጎች መሆናቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

የጂቡቲ የአገር ውስጥ ሚንስትር ኑህ ሐሰን ትናንት ምሽት በሁለቱ ብሔር ተወላጆች መካከል የተከሰተውን ግጭት መንግሥት "እንደማይታገሰው" ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።ሚኒስትሩ በግጭቱ ወቅት መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው እና ፖሊስ ላይ ድንጋይ መወርወሩንም አክለው ገልጸዋል።የዓይን እማኞች በግጭቱ የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን ይናገራሉ።የጂቡቲ የአገር ውስጥ ሚኒስትር በበኩላቸው ዜጎች ከማንኛውም ግጭት እንዲታቀቡ ጥሪ አቅርበው፤ መንግሥት ግጭት የሚቀሰቅሱ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል።

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ በአፋር እና በሶማሌ ክልል ተወላጆች መካከል በገርባ ኢሴ ከተማ ግጭት ተቀስቅሶ በርካቶች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።ይህንንም ተከትሎም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የክልሉን ተወላጆች ሕይወት ለመታደግ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ እንደሚወስዱ ተናግረው ነበር።በአፋር እና በሶማሌ ክልል መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ግጭቶች ይከሰታሉ።ይህንንም ተከትሎ በተደጋጋሚ በተነሳ ግጭት የንጹሀን ዜጎች ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ ተፈናቅለዋል።

[BBa