🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ዋላችሁ አንዳንዴ አሁን ባለንበት ህይወት ደስተኛ አንሆንም፤ ነገ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ዋላችሁ

አንዳንዴ አሁን ባለንበት ህይወት ደስተኛ አንሆንም፤ ነገር ግን በአለም ላይ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች የእኛን ህይወት ለመኖር በፀሎት ላይ ናቸው።

በእርሻ ውስጥ ያለ አንድ የገበሬ ልጅ ከጭንቅላቱ በላይ የሚበር አውሮፕላን አይቶ መብረርን ያልማል። ነገር ግን የአውሮፕላን አብራሪው ካፒቴን የገበሬዎቹን ጎጆዎች ተመልክቶ በሰላም ወደ ቤቱ መመለስን ይመኛል።

ህይወት ማለት ያ ነው። ያለንን እንደሰትበት፤ እናመስግንበት። ሀብት የደስታ ምንጭ ቢሆን ባለፀጎች በመንገድ ላይ በነሱ ነበር። ነገር ግን ደሃ ህፃናት ናቸው ያን ሲያደርጉ የሚታየው።

ስልጣን ደንነትን የሚያረጋግጥ ቢሆን መሪዎች ያለ አጃቢ ይሄዱ ነበር። ግን ቀላል ህይወት የሚኖሩት ናቸው በነፃነት ሲንቀሳቀሱ ውለው የሰላም ዕንቅልፍ የሚተኙት።

ቆንጆና ታወቂ መሆን አስደሳች ግንኙነት ለመፍጠር ዋስትና ቢሆኑ ታዋቂ ሰዎች ሁሉ የተሳካ ትዳር ይኖራቸው ነበር።

በጠቅላላው አሁን እየኖርነው ያለው ህይወት ከምንመኘው ሌላ ህይወት የተሻለ ቢሆን እንጂ አያንስም። ከሁሉም ከሁሉም ደሞ የእኛን ህይወት ለመኖር ሌት ከቀን ፈጣሪያቸውን የሚለምኑም እንዳሉ አንርሳ።
ለተደረገለን ሁሉ እናመስግን


Kogoese