🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ እውነተኛ አፈ ታሪክ ነው በድሮ ጊዜ አንድ አግኝቶ ያጣ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ

እውነተኛ አፈ ታሪክ ነው

በድሮ ጊዜ አንድ አግኝቶ ያጣ ባለፀጋ ሰውዬ በአገሪቱ አሉ የተባሉ ባለሀብት ሰው ጋር ይሄድና

"ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡

ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከዶሮ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡

ነዳያኑም "ቆዳዋ" አለ፡፡

ባለጠጋውም "እውነትም አግኝተክ ያጣክ ነህ፤ በሉ ከእህሉ ስፈሩለት፤ ከከብቶቹም የሚበቃውን ያህል ስጡት ብሎ አሰናበተው፡፡

ይህ ሰው ወደ ቀየው ሲመለስ አንድ ወዳጁ ይሄን ሁላ ሀብት ከየት እንዳገኘ ይጠይቀዋል፡፡ ተመፅዋቹም ሁሉን ነገር ነገረው፡፡ ከዛ ባልንጀራው እንደሱ ሀብት ለመቀበል ወደ ባለጠጋው ሰው ሄደ፡፡

እዛም እንደደረሰ "ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡


ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከበሬ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡

ነዳያኑም "ቆዳው" አለ፡፡

ባለጠጋውም አንተ አጭበርባሪ ነክ ብሎ በባዶ ሰደደው፡፡

የፈለገ ብንቸገር መዋሸት ግን አይሆኑ ውድቀት ላይ ይጥለናል፡፡

መልካም ውሎ፤ ቸር ያሰማን
⓾𝕥𝕙 𝕗𝕦𝕟 𝕥𝕙𝕖 𝕓𝕖𝕤𝕥 𝕨𝕒𝕪 𝕠𝕗 𝕝𝕖𝕒𝕣𝕚𝕟𝕘
Kogoese