Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን '• አንዳንድ ቀን የምንፈልገዉን እናገኛለን ወይም አናገኝም ወይም ደግሞ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ሰላም ለእናንተ ይሁን

"• አንዳንድ ቀን የምንፈልገዉን እናገኛለን ወይም አናገኝም ወይም ደግሞ ከዛ በላይ የሚበልጥ ነገር እናገኛለን፡፡

• ያለህ ብቸኛ ነገር እራስህ ብቻ ብትሆንስ? ያ ብቸኛ ነገር ላንተ በቂ ቢሆንስ?

• እራስህን በአዲስ መልክ ለመስራት አትፍራ!

• ድንገት ተነስተህ ቢራቢሮ አልሆንክም፤እድገት ሂደት ነዉና!

• ይገለኛል ያልሽዉን ነገር አሸንፈሽ በህይወት አለሽ፡፡ስለዚህ ዘዉድሽን አስተካክለሽ ልክ እንደንግስት ወደፊት ተራመጂ!

• ህይወት አጭር ናት፤ ጉዞ አድርግ ፣ ጫማ ግዛ ፣ በወጣትነት ሚስትህ ደስ ይበልህ፣ ኬክ ብላ ጣፋጭ ነገር ካልተስማማህ ወደ ሸንኮራ ቀይረው !

• አንቺ ማለት ብዙዎቹ ሴቶች በህልማቸዉ እንኳን ቢደርስባቸዉ የማይችሉትን ፈተና ያለፍሽ ጠንካራ ሴት ነሽ፡፡ መቼም ቢሆን ይህንን እንዳትረሺ!

• ሰዎች ፅጌረዳን እሾሃም ወይም ዉብ ቢሏት አይበርዳት አይሞቃት!

• የሆነ ሰዉ አበባ እንዲያመጣልሽ አትጠብቂ፡፡የራስሽን አትክልት ተክለሽ ነፍስሽን አስዉቢያት!

• ህልምህ ኤክስፓየር ቀን የለዉም ስለዚህ ትንፋሽህን ስበህ እንደገና ሞክር!

•ከሁሉም በፊት ግን ብዙዎች ሊደርሱበት አቅደው ፣ ሊያዩት ተመኝተው ፣ ሊያጣጥሙት ጓጉተው ነገር ግን ሳይደርሱበት ከቀሩት ዛሬ ላይ አንተ እንድትገኝ ስለተፈቀደልክ ፈጣሪክን አመስግነው

ቸር ያሰማን

kogoese